መዝሙር (የሥላሴን መንበር) December 17, 2017

  • Print

የሥላሴን መንበር

የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት
ኪሩቤል በደመና ዙፋኑን ይዘውት
ድንግልን ከመሃል ሚካኤልን ከፊት
አእላፍ መላእክት ሲሰግዱ በፍርሃት
እዩት ተመልከቱት የሰማዩን ድምቀት
እዩት ተመልከቱት የሰማዩን አባት

የሥላሴን መንበር ቅዱሳን ከበውት
እያሸበሸቡ የሰማይ መላእክት
ካህናተ ሰማይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሲሉ
ይህን ልዩ ክብር ሊያዩ የታደሉ
በጽድቅ ሥራቸው በምድር ይታያሉ (2)

የቅዱሳን ኅብረት የቅዱሳን ሀገር
ሲያወድስ ይኖራል የሥላሴን ክብር
ጽድቅና ርኅራኄ የተመላ ሰማይ
እግዚአብሔር ያድለን በትንሣኤ እንድናይ (3)