መዝሙር (አርሴማ) December 17, 2017

አርሴማ

ጽኑ ሰማዕት የእምነት አርበኛ
አርሴማ ነይ ነይ ወደኛ

ነይ ነይ ቅዱስ አትናትዮስ ነይ ነይ በስዕለት ያገኙሽ
›› ›› ብሉይን ከሀዲስ ›› ›› ጠንቅቀሽ የተማርሽ
›› ›› በፍፁም ትህትና ›› ›› በጸሎት የተጋሽ
›› ›› አርሴማ ልዩ ነሽ ›› ›› አምላክ የመረጠሸ

አዝ…

ነይ ነይ ውበትም ሀሰት ነው ነይ ነይ ደም ግባትም ከንቱ
›› ›› ንብረት ትዳር ሁሉ ›› ›› አላፊ ውዕቱ
›› ›› ንግስት መባልን ›› ›› በፍጹም ሳትሻ
›› ›› አለምን በመናቅ ›› ›› ገባች ወደዋሻ

አዝ…

ነይ ነይ አረመኔው ድርጣድስ ነይ ነይ ቢያሰቃይሽም
›› ›› ውበቴ ክርስቶስ ›› ›› ነው ብለሽ ሰበክሽ
›› ›› አንገትሽን ለሰይፍ ›› ›› አሳልፈሽ ሰጠሸ
›› ›› ክብርሽም ተገልጾ ›› ›› ለአለም አበራሽ

አዝ…

ነይ ነይ አርአያ ልትሆኝን ነይ ነይ ለእኛ ለሁላችን
›› ›› ፈፅመሽ አሳየሽ ›› ›› ታላቅ ተጋድሎሽን
›› ›› ይህን አለም ድል መንሳት ›› ›› አቅቶናል እና
›› ›› አርሴማ አትለይን ›› ›› በእምነት እንድንጸና