መዝሙር (አንቺ የወይን ሐረግ) December 24, 2017

  • Print

አንቺ የወይን ሐረግ 
አንቺ የወይን ሐረግ ድንግል ልምላሜሽ የበዛ /፪/ 
ምግብ ሆኖ /፪/ ተሰጠን ፍሬሽ ለእኛ ቤዛ /፪/ 
በአንቺ ሰማይነት ድንግል የወጣው ፀሐይ 
ብርሃን ነው /፪/ ለጻድቃን ስሙም አዶናይ 
አዝ ... 

ፊደል ትመስያለሽ ድንግል ወንጌል ትወልጃለሽ 
ለመላእክት/፪ አ/ የማይቻል ነበልባሉን የያዝሽ 
አዝ ... 

የመሶብ ምሳሌ ድንግል የኮከብ መገኛ 
በነፍሳችን በሥጋችን እንዳንጠፋ አንቺ አለሽን ለእኛ