መዝሙር (አድኝኝ እናቴ ከስጋ ፈተና) February 18, 2018

  • Print


  አድኝኝ እናቴ ከስጋ ፈተና
  ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አራቀምና
  ሸክሜ የከበደ ብቸኛ ሆኛለሁ
  አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ( 2)

የአማኑኤል እናት የተዋህዶ አክሊል
አትጥፊ ከመሃል እንድትሆኝን ኃይል
ምንም ቢበዛብሽ የኛ ጉስቁልና
ከእኛ ጋራ ከሆንሽ አለን ቅድስና (2)

  አድኝኝ እናቴ ከስጋ ፈተና
  ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አራቀምና
  ሸክሜ የከበደ ብቸኛ ሆኛለሁ
  አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ( 2)

ተስፋዬ ነሽና እመካብሻለሁ
ግራ ቀኝም አልል ምርኮኛሽ ሆኛለሁ
ስቅበዘበዝ አይቶ ተስፋ የሠጠኝ
እግዚአብሔር ይመስገን ካንቺ ያስጠጋኝ (2)

  አድኝኝ እናቴ ከስጋ ፈተና
  ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አራቀምና
  ሸክሜ የከበደ ብቸኛ ሆኛለሁ
  አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ( 2)

በሥጋ ደክሜ በነፍሴ እንዳልጠፋ
እማጸንሻለሁ ድንግል የኔ ተስፋ
የመንግስቱ ወራሽ እንድሆን አድርጊኝ
መልካም ስራ መስራት እኔን አስተምሪኝ(2)

  አድኝኝ እናቴ ከስጋ ፈተና
  ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አራቀምና
  ሸክሜ የከበደ ብቸኛ ሆኛለሁ
  አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ( 2)

አንቺ የሌለሽበት ጉባዔው ባዶ ነው
በቁም የደረቀ ሕይወት የተለየው
ከመሐከል ገብተሽ ሙይ የጎደለውን
ሰርጉ ተደግሷል ጎብኝልን ጓዳውን(2)

  አድኝኝ እናቴ ከስጋ ፈተና
  ሥጋዬ ከኃጢአት ከቶ አራቀምና
  ሸክሜ የከበደ ብቸኛ ሆኛለሁ
  አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ( 2)