የጉባኤ መዝሙር (ልመናዬን ስማ) February 17, 2018


  ልመናዬን ስማ ቃሌንም አድምጥ
 እውነተኛው አምላክ ሰላምህን ስጥ

ክርስቲያኖች ሁሉ ትእዛዙን አክብሩ
ምስጋናን አቅርቡ ስገዱ ዘምሩ
የጌታን አመጣጥ ለአለም ንገሩ
ደቀ መዛሙርቱ ወንጌል አስተምሩ

  ልመናዬን ስማ ቃሌንም አድምጥ
 እውነተኛው አምላክ ሰላምህን ስጥ

በመልካም የሚሄድ ጽድቅን የሚሠራ
የፈጣሪውን ስም በከንቱ የማጠራ
ይጎበኛል በምድር በሰማዩም ሥፍራ
በቀኝ ይቀመጣል ከቅዱሳን ጋራ

  ልመናዬን ስማ ቃሌንም አድምጥ
 እውነተኛው አምላክ ሰላምህን ስጥ

ስለ ጠላቶቼ በጽድቅህ ምራኝ
በጥል ቃል ከበቡኝ ተሰለፉብኝ
መሐሪ ይቅር ባይ መጠጊይያ ሁነኝ
አንተ በቸርነት ይቅርታን ስጠኝ