መዝሙር (ሞተሃልና ስለእኔ) February 25, 2018

  • Print

ሞተሃልና ስለእኔ ምንም ሳይኖርህ ጥፋት
ተከሰህ ተወቅሰህ በጲላጦስ ፊት
ኢየሱስ አምላከ ምህረት ስብሃት ለከ

ስላላወቁህ አንተን የአለም መድኃኒት መሆክን
መቱት በጭካኔ ብርሃን ፊትህን
ኢየሱስ አምላከ ምህረት ስብሃት ለከ

የአንተን መንገላታት ሁልጊዜ ያሳዝነኛል ሲወራ
በመስቀል ላይ ሆነህ ያየኸው መከራ
ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ ስብሐት ለከት ስብሐት ለከ

ከልዑል ቦታ ወርደህ ፈጣሪ ፍጡራን አምላክ
በሰው ፊት ተዋርደህ ስለ ሰው የሞትክ
በመስቀል ላይ ተጠማሁ እያልክ ስብሐት ለከ

መሐሪ ጌታ አሁንም እንደ ቸርነትህ ብዛት
የእኛን በደል ሁሉ ሳትመለከት
አድነን ከዳግም ሞት ስብሐት ለከ