መዝሙር (ለዚህ ላደረሰን) October 6, 2019

  • Print


 ለዚህ ላደረሰን በሰላም በጤና /፪/
 ሃሌ ሃሌ ሉያ /፪/ እናቅርብ ምሥጋና

ሥራችንን ዐይቶ በደላችንን
ይህን ሁሉ ታግሦ ለዚህ ላበቃን
 ሃሌ ሃሌ ሉያ /፪/ እናቅርብ ምሥጋና

አንተ በምሕረትህ ለዚህ ላደረስከን
የአንድ ቀንም ዕድሜ ስለጨመርክልን
ቸሩ አምላካችን ሆይ አንተን እናመሥግን
 ሃሌ ሃሌ ሉያ /፪/ እናቅርብ ምሥጋና

ጌታ አምላካችን ሆይ ተስፋችን አንተው ነህ
እምነታችን ይጽና ፈቃድህ ይሁንልን
አንተ በምሕረትህ በይቅርታህ ጎብኘን
 ሃሌ ሃሌ ሉያ /፪/ እናቅርብ ምሥጋና

 ለዚህ ላደረሰን በሰላም በጤና /፪/
 ሃሌ ሃሌ ሉያ /፪/ እናቅርብ ምሥጋና