መዝሙር (አልተወኝም ጌታ) March 15, 2020

  • Print

 አልተወኝም ጌታ ለካስ ይወደኛል/፪/
 ዛሬም ስበድለው ልጄ ነህ ይለኛል
 ዛሬም ስበድለው ልሄ ነሽ ይለኛል

በበደል ጉራንጉር በሐጢአት ጫካ
ብጠፋበት እንኳን አልተወኝም ለካ
ዛሬም ልጄ ብሎ ዳግም ይጠራኛል
ለካስ አልጠላኝም ጌታ ይወደኛል (፪)

 አልተወኝም ጌታ ለካስ ይወደኛል/፪/
 ዛሬም ስበድለው ልጄ ነህ ይለኛል
 ዛሬም ስበድለው ልሄ ነሽ ይለኛል

ለሥልጣን ለክብሬ ብዬ ስክደው
ለገንዘብ አድልቼ እኔ ስረሳው
ለእኔ ያለው ፍቅር አልቀነሰብኝም
ዛሬም ይወደኛል ጌታ አልጠላኝም (፪)

 አልተወኝም ጌታ ለካስ ይወደኛል/፪/
 ዛሬም ስበድለው ልጄ ነህ ይለኛል
 ዛሬም ስበድለው ልሄ ነሽ ይለኛል

ታዲያ ለዚህ ፍቅሩ ለሌለው ወሰን
ከጭንጫ መቃብር ላወጣኝ እኔን
በሕይወቴ ሁሉ ፍፁም ለመራኝ
ክብርና ምስጋናን አቀርባለሁኝ (፪)