መዝሙር (ሰአሉ ለነ) January 31, 2021 (Second Mezmur)

  • Print

 ሰአሉ ለነ ቅዱሳን መላእክት /፪/
 ሰአሉ ለነ ጻድቃን ሰማእታት
 ኀበ አምላከ ምህረት ሰአሉ ለነ

 ለምኑልን ቅዱሳን መላእክት /፪/
 ለምኑልን ጻድቃን ሰማእታት
 ወደ አምላከ ምህረት ለምኑልን

አንተ የመረጥከውን ማን ይከሳል
ያጸደቅከውን ማን ይወቅሳል
ለሚገባው ክብርን መስጠት
ታዟልና በመጻሕፍት
ያከበርካቸው ባሪያዎችህን
እናከብራለን ቅዱሳንህን

 ሰአሉ ለነ ቅዱሳን መላእክት /፪/
 ሰአሉ ለነ ጻድቃን ሰማእታት
 ኀበ አምላከ ምህረት ሰአሉ ለነ

 ለምኑልን ቅዱሳን መላእክት /፪/
 ለምኑልን ጻድቃን ሰማእታት
 ወደ አምላከ ምህረት ለምኑልን

ሁሉ መዳንን እንዲይዙ
የሚላኩ የሚያግዙ
ሰርክ ፊትህ እየቆሙ
ጥዑም ቅዳሴን እያሰሙ
በምስጋናቸው የሚያከብሩህን /፪/
እናከብራለን መላእክትህን /፪/

 ሰአሉ ለነ ቅዱሳን መላእክት /፪/
 ሰአሉ ለነ ጻድቃን ሰማእታት
 ኀበ አምላከ ምህረት ሰአሉ ለነ

 ለምኑልን ቅዱሳን መላእክት /፪/
 ለምኑልን ጻድቃን ሰማእታት
 ወደ አምላከ ምህረት ለምኑልን

ጤዛ ልሰው ዳዋ ጥሰው
ዋዕይ ቁሩንም ታግሰው
በየፉርክታው በየ ዱሩ
ሌጦ ለብሰው እየዞሩ
በጽናታቸው ያከበሩህን /፪/
እናከብራለን ጻድቃንህን /፪/

 ሰአሉ ለነ ቅዱሳን መላእክት /፪/
 ሰአሉ ለነ ጻድቃን ሰማእታት
 ኀበ አምላከ ምህረት ሰአሉ ለነ

 ለምኑልን ቅዱሳን መላእክት /፪/
 ለምኑልን ጻድቃን ሰማእታት
 ወደ አምላከ ምህረት ለምኑልን

እንደሚታረድ በጎች ሆነው
አንገታቸውን ለሰይፍ ሰጥተው
ስለ ስምህም እየተጠሉ
ከአንበሳ ጋራ እየታገሉ
በተጋድሏቸው ያከበሩህን /፪/
እናከብራለን ሰማዕታትህን /፪/

 ሰአሉ ለነ ቅዱሳን መላእክት /፪/
 ሰአሉ ለነ ጻድቃን ሰማእታት
 ኀበ አምላከ ምህረት ሰአሉ ለነ

 ለምኑልን ቅዱሳን መላእክት /፪/
 ለምኑልን ጻድቃን ሰማእታት
 ወደ አምላከ ምህረት ለምኑልን

ከሕያው ቃልህ እየጠቀሱ
መናፍቃንን ድል የነሡ
በገዛ ደምህ የዋጀሃትን
ቤተ ክርስቲያንን የጠበቋትን
በሕይወታቸው ያስደሰቱህን /፪/
እናከብራለን ቅዱሳንህን /፪/

 ሰአሉ ለነ ቅዱሳን መላእክት /፪/
 ሰአሉ ለነ ጻድቃን ሰማእታት
 ኀበ አምላከ ምህረት ሰአሉ ለነ

 ለምኑልን ቅዱሳን መላእክት /፪/
 ለምኑልን ጻድቃን ሰማእታት
 ወደ አምላከ ምህረት ለምኑልን