መዝሙር (ሰአሊ ለነ ቅድስት) February 28, 2021 (First Mezmur)

  • Print

 ሰአሊ ለነ ቅድስት እንልሻለን/ ፪ /
 እንደ ኤፍሬም እንደ አባታችን
 ለምኝልን እመቤታችን / ፪ /

ተስፋቸው ነሽና ለፍጥረት ዓለም
እየተመኩብሽ እስከ ዘለዓለም
ኃጢአታቸው ተደምስሶላቸው
በአንቺ ጸሎት ዳነች ሕይወታቸው

 ሰአሊ ለነ ቅድስት እንልሻለን/ ፪ /
 እንደ ኤፍሬም እንደ አባታችን
 ለምኝልን እመቤታችን / ፪ /

ስምሽም ስልጡን ነው በእግዚአብሔር መንበር
ቃል ኪዳን ገባልሽ ዓለሙን ሊምር
በአንቺ ጸሎት ይተማመናሉ
ጠዋት ማታ ቅድስት ሆይ ይላሉ

 ሰአሊ ለነ ቅድስት እንልሻለን/ ፪ /
 እንደ ኤፍሬም እንደ አባታችን
 ለምኝልን እመቤታችን / ፪ /

ዓለም ስትዋጋን በምኞት ስለት
ነፍሳችን ስትዝል ሲከብዳት ኃጢአት
ጨልሞብን ግራ ሲገባን
ብርሃናችን ነይ እናታችን

 ሰአሊ ለነ ቅድስት እንልሻለን/ ፪ /
 እንደ ኤፍሬም እንደ አባታችን
 ለምኝልን እመቤታችን / ፪ /

የልባችን ሐዘን እጅጉን ከብዶናል
በደላችን በዝቶ መቆም ተስኖናል
እንደ ኤልሳቤጥ እንደ ዘመድሽ
ደስ አሰኝን ይሰማን ድምፅሽ

 ሰአሊ ለነ ቅድስት እንልሻለን/ ፪ /
 እንደ ኤፍሬም እንደ አባታችን
 ለምኝልን እመቤታችን / ፪ /