መዝሙር (እልል በሉ) December 3, 2023 (First Mezmur)

  • Print

እልል በሉ

==============
 እልል በሉ በአንድነት ዘምሩ
 አመስግኑ ለክብሩ ዘምሩለት
 እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ

በኃጢያት ባርነት ስንኖር ተገዝተን
ከቤቱ ስንርቅ ትእዛዙን አፍርሰን
አይቶ ዝም ላላለን ጠላቶቹ ስንሆን
ውለታው ብዙ ነው ክብር ለዕርሱ ይሁን/2/

 እልል በሉ በአንድነት ዘምሩ
 አመስግኑ ለክብሩ ዘምሩለት
 እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ

ራሱን አዋርዶ እኛን አከበረን
ሥጋውና ደሙን ብሉ ጠጡ አለን
መልካም እረኛ ነው የሚያሳጣን የለም
ምስጋና ይድረሰው ለመድሐኔአለም/2/

 እልል በሉ በአንድነት ዘምሩ
 አመስግኑ ለክብሩ ዘምሩለት
 እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ

ሕይወቱን የሰዋ እንደ አምላክ ማን አለ
ለሰው ልች ብሎ በመስቀል የዋለ
ፍቅሩ አይለካ አያልቅም ቢወራ
ከሰማያትወርዶ ሆነ ከእኛ ጋራ/2/

 እልል በሉ በአንድነት ዘምሩ
 አመስግኑ ለክብሩ ዘምሩለት
 እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ

ሥራውን እናድንቅ እንዲህ ለወደደን
ከማያልቀው ፍቅሩ በረከት ላደለን
ለማይነገረው ለአምላክ ስጦታ
ውዳሴን እናቅርብ እንዘምር በእልልታ /2/

 እልል በሉ በአንድነት ዘምሩ
 አመስግኑ ለክብሩ ዘምሩለት
 እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ