መዝሙር (በማህፀን ቅኔ) December 10, 2023 (Second Mezmur)

  • Print

በማህፀን ቅኔ

==============
 በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
 በተራራማ ሃገር በኤፍሬም ከተማ
 ዩሐንስ ይናገር በረሃ ያደገው
 ድንግል ስትናገር ምን እንዳዘለለው /2/

የእናቱ ማህፀን የቅኔ ርስት ሆነች
ድንግል የአምላክ እናት ፊቱ ስለቆመች
በሃሴት ዘለለ ዘመረ በደስታ
ከድንግል ሲወጣ ታላቁ ሰላምታ

 በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
 በተራራማ ሃገር በኤፍሬም ከተማ
 ዩሐንስ ይናገር በረሃ ያደገው
 ድንግል ስትናገር ምን እንዳዘለለው /2/

በድንግል ማህፀን ስላየ ጌታውን
ከመወለድ ቀድሞ ሰማነው መዝሙሩን
ትንቢቱ ሲፈፀም በሆዷ ሲነግስ
ሰገደ ለአምላኩ የስድስት ወር ፅንስ

 በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
 በተራራማ ሃገር በኤፍሬም ከተማ
 ዩሐንስ ይናገር በረሃ ያደገው
 ድንግል ስትናገር ምን እንዳዘለለው /2/

ጀመረ ስብከቱን ገና ሳይወለድ
ተፈጥሮ መች ቻለ ነብዩን ለማገድ
አፉ ተከፈተ በታላቅ ምስጋና
በእናቱ ማህፀን ድምጽን አሰማና

 በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
 በተራራማ ሃገር በኤፍሬም ከተማ
 ዩሐንስ ይናገር በረሃ ያደገው
 ድንግል ስትናገር ምን እንዳዘለለው /2/

የዩሐንስ እና ኤልሳቤጥ ገረማት
ልጇ በማህፀን ቅኔ ሲቀኝባት
ድምጿን ከፍ አደረገች አለም እንዲሰማ
ሞላት መንፈስ ቅዱስ ለመዝሙር ለዜማ

 በማህፀን ቅኔ ለማርያም ተሰማ
 በተራራማ ሃገር በኤፍሬም ከተማ
 ዩሐንስ ይናገር በረሃ ያደገው
 ድንግል ስትናገር ምን እንዳዘለለው /2/