Beza Kulu Sunday School 18th Year Anniversary

ቅዳሜ ጁን 7 ቀን 2014 ዓ.ም. 3pm ጀምሮ የጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ቤዛ ኩሉ ሰንበት ትምህርት ቤት እና የሰበካ ጉባኤው አስተዳደር በመተባባር ልዩ መርሃ ግብር አዘጋጅተዋል። በዕለቱም የሰንበት ትምህርት ቤታችንን ፲፰ኛ ዓመት ዓመታዊ በዓል በተለመደው ሁኔታ በድምቀት እናከብራለን። 
በዚህም መርሃ ግብር 

- የስብከተ ወንጌል፣ 
- ያሬዳዊ ዝማሬ፤ 
- የስነ ጽሑፍ እና ሌሎች መርሃ ግብሮች ሲኖሩን፤  

የቤተ ክርስቲያናችንም ሰበካ ጉባኤም ላለፉት በርካታ ወራት ምዕመናን ለሐይማኖታችን ያደረግነውን ተጋድሎ ለማስታወስ፤ በዚህ ፈታኝ ወቅትም የቤተ ክርስቲያናችን ካህናት እና ዲያቆናት ላሳዩት የእምነት ጽናት እና የሐይማኖት ቁርጠኛነት ምስጋና ለማቅረብ የእራት ግብዣ ምሽት አዘጋጅቷል ። 

ምዕመናን በእራት ምሽቱ ላይ ስለ ቤተ ክርስቲያናችንን የወደፊት ራዕይ የጠረጴዛ ውይይት እያደረጉ ሃሳብ እንዲያመነጩ የሚደረግ ሲሆን በመርሃ ግብሩ መገባደጃ ላይም ለየት ያሉ ዕቃዎች ለጫራታ ቀርበው ለቤተ ክርስቲያናችን የገቢ ማሰባሰቢያ ይደረጋል። 

በዚሁ አጋጣሚ እርስዎም ላልሰሙ ምዕመናን ይህንን አሰምተው ዕለቱን በታላቅ ድምቀት እንድናከብረው የሰንበት ትምህርት ቤቱ እና የሰበካ ጉባኤው አስተዳደር መንፈሳዊ ጥሪውን ያስተላልፋል

Address:
St. Paul Student Center
2017 Buford Ave, St Paul, MN 55108

ቅዳሜ 3pm ጀምሮ