Filter
  • ሥርዓት ዘሰሙነ ፍልሰታ

    ነሐሴ 1 ቀን 2006 ዓ.ም.

    በክርስቶስ ደም የተመሠረተችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዓመት ውስጥ የተለያዩ ሃይማኖታዊና መንፈሳዊ የሆኑ ተግባራትን ታከናውናለች፡፡ ዋጋ የሚያሰጡ፣ ከፈጣሪ የሚያስታርቁ በዓላትንም ታከብራለች፤ ለምሳሌ በዓለ ልደት፣ በዓለ ጥምቀት፣ በዓለ ትንሣኤ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ለእነዚህ በዓላት የተለያየ የአከባበር ሥርዓት አላቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ቤተ ክርስቲያናችን ኃጢአትን የሚያስተሰርዩ፣ ከፈጣሪ የሚያስታርቁ፣ ሥጋ ለነፍስ እንድትገዛ የሚያግዙ፣ ከባሕርየ እንስሳ ወጥተን ሰማያውያን መላእክትን እንድንመስላቸው...