የንባብ ምልክቶች

መስከረም 6 ቀን 2007 ዓ.ም5

 ካለፈው የቀጠለ

2. ቀደሰ -- አመሰገነ 3. ገብረ--- ሠራ፣ ፈጠረ

ይቄድስ --- ያመስግን ይገብር --- ይሠራል

ይቀድስ ---- ያመሰግን ዘንድ ይግበር ---- ይሠራ ዘንድ

ይቀድስ ---- ያመስግን ይግበር ---- ይሥራ

  • ቀድሶ / ቀድሶት/ --- ማመስገን ገቢር /ገቢሮት/ --- መሥራት

ቀዳሲ ---- ያመሰገነ ገባሪ ---- የሠራ

ቀዳስያን ---- ያመሰገኑ ገባርያን ---- የሠሩ

ቀዳሲት --- ያመሰገነች ገባሪት ---- የሠራች

ቀዳስያት --- ያመሰገኑ / ሴ/ ገባሪያት ---- የሠሩ /ሴ/

ቅዱስ --- ምስጉን ግቡር ---- የተሠራ

ቀዳሲ --- አመስጋኝ ገባሪ ---- ሠሪ

ቅዳሴ --- ምስጋና ግብር ---- ሥራ

መቅደስ --- ማመስገኛ ግብረት ---- አሠራር / አደራረግ/

ቅድስት ---- የተመሰገነች ምግባር ----- በጎ ሥራ

ተግባር --- ሥራ

እንደ ቀደሰ የሚረቡ ግሶች ሰብሐ፣ ጸለየ ናቸው፡፡

እንደ ገብረ የሚረቡ ግሶች ሠምረ፣ ኀብረ፣ ነጽሐ ወዘተ . . . ናቸው፡፡


4. አእመረ --- አወቀ 5. ባረከ --- ባረከ /አመሰገነ

የአምር ---- ያውቃል ይባርክ --- ይባርካል /ያመሰግናል/

ያእምር ---- ያውቅ ዘንድ ይባርክ --- ይባርክ ዘንድ

ያእምር --- ይወቅ ይባርክ --- ይባርክ

  • አእምሮ / አእምሮት/ --- ማወቅ * ባርኮ / ባርኮት/ --- መባረክ

አእማሪ --- ያወቀ ባራኪ ---- የባረከ

አእማርያን --- ያወቁ /ወ/ ባራክያን --- የባረኩ

አእማሪት --- ያወቀች ባራኪት ---- የባረከች

አእማርያት --- ያወቁ /ሴ/ ባራክያት --- የባረኩ /ሴ/

እሙር --- የታወቀ ቡሩክ --- የተባረከ

አእማሪ --- አዋቂ ባራኪ ---- የሚባርክ

ማእምር ---- የሚያውቅ ቡራኬ ----ቡራኬ

አእምሮ --- እውቀት በረከት --- በረከት

  • አእመረን የሚመስሉ፣ አጥረየ፣ አመንተወ፣ አመክነየ፣ አመድበለና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

  • እንደ ባረከ የሚረቡ ማህረከ፣ ፃመወ፣ ሳቀየ፣ ወዘተ . . . የመሳሰሉት ናቸው፡፡

6. ሤመ ---ሾመ                        7. ብሀለ --- አለ

ይሠይም ---ይሾማል                     ይብህል --- ይላል

ይሢም --- ይሾም ዘንድ                 ይብሃል --- ይል ዘንድ

ይሢም ---- ያሹም                     ይብሃል ---- ይበል

  • ሠይም / ሠይሞት/ --- መሾም    * ብሂል/ ብሂሎት/----ማለት

ሠያሚ --- የሾመ                                በሀሊ---- ያለ

ሠያምያን --- የሾሙ                             በሀልያን --- ያሉ

ሠያሚት --- የሾመች                            በሀሊት --- ያለች

ሠያምያት --- የሾሙ /ሴ/                       በሀልያት --- ያሉ /ሴ/

ሥዩም ---- የተሾመ                            ብሂል --- የተባለ

ሠያሚ ----ሿሚ                                ባሃሊ ---- የሚል

ሢመት --- ሹመት                              ባህል --- አባባል

8. ቆመ --- ቆመ

ይቀውም --- ይቆማል

ይቁም ----- ይቆም ዘንድ

ይቁም --- ይቁም

  • ቀዊም/ ቀዊሞት/ --- መቆም

ቀዋሚ ---- የሚቆም

ቀዋምያን ---- የሚቆሙ

ቀዋሚት ----- የምትቆም

ቀዋምያት ---- የሚቆሙ /ሴ/

ቅውም --- የሚቆም

ቀዋሚ ---- ቋሚ

ቁመት ---- ቁመት

  • ቆመን የሚመስል ሖረ፣ ሞርቅሐ / ላጠ/ ወዘተ . . . ናቸው፡፡

ማስታወሻ፣ የቆሙ፣ የቆመች፣ ያመሰገኑ፣ ያመሰገነች የምንለው ግሡ በቀዳማይ / በሃላፊ/ ስለረባ እና ቅጽሎች እንደመሆናቸው ሁሉ “ የ” የሚለውን ፊደል ለማመልከት ነው እንጂ ምን ጊዜም ለሃላፊ ወይም ለትንቢት ተብሎ ቅጽልን መከፋፈል አይደለም፡፡ ዘቆመት ስንልም ትርጉሙ ቀዋሚ ከሚለው ጋር አንድ ነው፡፡ የቆመች፣ ቋሚ ማለት ነውና፡፡


6.2 ሕገ ወጥ አካሄድ ያላቸው ግሶች፡፡ (Irregular Verbs)

ቀዳማይ ካልአይ ዘንድ ትእዛዝ

ወሀበ / ሰጠ/ ይውህብ፣ ይሁብ የሀብ የሀብ

ክህለ / ቻለ/ ይክል / ይክህል/ ይክሀል ይክሀል

ብህለ/ አለ/ ይብል ይበል ይበል

ይቤ / አለ/ ይብል ይበል ይበል

ርእየ / አየ/ ይርኢ ይርአይ ይርኢ / ይርእዪ/

ወድቀ / ወደቀ/ ይወድቅ ይደቅ ይደቅ

  • ድርጊቱ በመካሄድ ላለ ( Continuous)ነገር መጠቀም የምንችለው በካልአይ ነው

ምሳሌ፣ ይመጽእ ውእቱ

        እንዘ ይመጽእ ውእቱ (እየመጣ ነው ሊመጣ ነው)

 

 

Read more http://www.eotcmk.org/site/--mainmenu-56/1559-2014-09-16-12-34-18