ሰበር ዜና:- በዝቋላ ገዳም ዳግም የእሳት ቃጠሎ ተቀሰቀሰ

ሰበር ዜና:- በዝቋላ ገዳም ዳግም የእሳት ቃጠሎ ተቀሰቀሰ አትም ኢሜይል

የካቲት 25 ቀን 2007 ዓ.ም.

በእንዳለ ደምስስ

abune gebre menfes kidus 01 በደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንድነት ገዳም በዛሬው እለት ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ በምሥራቅ አቅጣጫ በሚገኘው ደን ዳግም የእሳት ቃጠሎ መቀስቀሱ ከገዳሙ አባቶች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡


በትናንትናው እለት ተቀስቅሶ የነበረው እሳት ከፍተኛ ርብርብ ተደርጎ ጠፍቶ የነበረ ቢሆንም በዛሬው እለት ተቀሰቀሰውን እሳት ለማጥፋት በገዳማውያኑ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በአሁኑ ሰዓት እሳቱ ደኑን እያወደመ በከፍተኛ ሁኔታ እየተቀጣጠለ እንደሚገኝ የገለጹት ገዳማውያኑ ከደብረ ዘይት አየር ኃይል ሄሊኮፕተር እንዲላክላቸው ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡

 

Read more http://www.eotcmk.org/site/-mainmenu-18/1755-2015-03-04-13-52-49