በኮንሶ ወረዳ ከ540 በላይ ሰዎች ተጠመቁ

በኮንሶ ወረዳ ከ540 በላይ ሰዎች ተጠመቁ አትም በኮንሶ ወረዳ ከ540 በላይ ሰዎች ተጠመቁ

አርባ ምንጭ ማእከል

ጥር 23 ቀን 2008 ዓ.ም

DSC04666

በጋሞ ጎፋ ሀገረ ስብከት በኮንሶ ወረዳ ኮልሜ፣ አባሮባ እና ዱሮ (አርፋይዴ፣ኦካይሌ፣ ጉላይዴ፣ ቦይዴ፣ ማደሪያ እና ካሻሌ) ቀበሌያት ከ540 በላይ ሰዎች ጥር 11 ቀን 2008 ዓ.ም ተጠመቁ፡፡የጋሞ ጎፋ ሀገረስ ስብከት በዕለቱ የማጥመቅ ሥነ-ስርዓቱን እንዲፈጽሙ ወደስፍራው ያቀኑትን ሁለት ካህናት የመደበ ሲሆን የኮንሶ ወረዳ ቤተ ክህነት፣ ማኅበረ ቅዱሳን አርባ ምንጭ ማእከል የስብከተ ወንጌል ክፍል፣ ሰባት የግቢ ጉባኤያት ዲያቆናት እና የካራት ወረዳ ማእከል በቦታው በመገኘት ጥምቀቱን አስተባብረዋል፡፡

ሀገረ ስብከቱ እና የኮንሶ ወረዳ ቤተ ክህነት ወንጌል ወዳልተዳረሰባቸው የገጠር መንደሮች የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በማስተማር ኢ-አማንያን እንዲጠመቁ ጥረት እያደረገ ሲሆን፤ ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከልና የአርባ ምንጭ ማእከልም ለስኬቱ እገዛ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ከድጋፎቹም ውስት የ2007 ዓ/ም አዲስ ተጠማቂያንን ለሚያስተምር አንድ ቋሚ የድጎማ መምህር ዋናው ማዕከል የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ ሲሆን፤ የአርባ ምንጭ ማእከልም በዱሮ እና ጉኛራ ቀበሌዎች አዳዲስ ሰንበት ት/ቤቶች እንዲደራጁ እና ሁለት የሰንበት ት/ቤቶች ተተኪ መምህራን እና አንድ ካህን በአካባቢ ቋንቋ ወንጌልን እንዲያስተምሩ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ በዚህም ምክንያት በርካታ ሰዎች እየተጠመቁ መሆኑ ታውቋል፡፡ በዚሁ እለት በዋናው ማእከል የተዘጋጀ ነጠላና የአንገት መስቀል ለሁሉም ተጠማቂያን የተሰጠ ሲሆን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል እጣን፣ ጧፍና ዘቢብም ድጋፍ ተደርጓል፡፡ በወረዳው በ2007 ዓ/ም በሁለት ዙር ከ980 በላይ ኢ-አማንያን ተጠምቀው የመንፈስ ቅዱስን ልጅነት ማግኘታቸው የሚታወስ ሲሆን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሁለንተናው አገልግሎት እየተሳተፉ እንደሚገኙ የወረዳው ቤተ ክህነትና የማእከሉ ስብከተ ወንጌል ክፍል አሳውቀዋል፡፡

በኮንሶ ወረዳ ከ540 በላይ ሰዎች ተጠመቁ በኮንሶ ወረዳ ከ540 በላይ ሰዎች ተጠመቁ በኮንሶ ወረዳ ከ540 በላይ ሰዎች ተጠመቁ በኮንሶ ወረዳ ከ540 በላይ ሰዎች ተጠመቁ

Read more http://www.eotcmk.org/site/-mainmenu-18/2068--540-