* በጾመ ፍልሰታ የሱባኤ ወቅት ሰዓታት ይቆማል፣ ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም ይተረጎማል፣ ቅዳሴ እና የሰርክ ጸሎት ይደርሳል

* በአዲስ ዓመት (በዘመን መለወጫ)፣ በልደት  በትንሣኤ እና ቤተ ክርስቲያናችን ባሏት ተጨማሪ ዐበይት በዓላት የተለያዩ መርሐ-ግብሮች ይከናወናሉ።

* በሰሞነ ሕማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሙሉ አገልግሎት ይሰጣል

 

ክርስትና

* ቤተ ክርስቲያናችን ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጀምሮ በርካታ ሕፃናት የጥምቀተ ክርስትና አገልግሎት አግኝተዋል።

 

ስብከተ ወንጌል እና መንፈሳዊ ትምህርት

* ዘወትር አርብ ስብከተ ወንጌል ይሰጣል

* ዘወትር ቅዳሜ መላ ምእመናንን የሚያሳትፍ የሰንበት ትምህርት ቤት መርሐ-ግብር ይደረጋል

* ዘወትር ቅዳሜ የአብነት ትምህርት እና መሠረታዊ የአማርኛ ቋንቋ ለወጣቶችና ለታዳጊ ሕፃናት ይሰጣል

* ዘወትር እሑድ ሃይማኖታዊና የሥነ-ምግባር ትምህርት ለሕፃናት እና ለወጣቶች ይሰጣል

 

ዕድር

* የቤተ ክርስቲያናችን አባላት የሆኑ ብቻ በአባልነት ተመዝግበው በኀዘናቸው ጊዜ መርጃ እንዲሆናቸው ታስቦ የተቋቋመው ዕድር ለአባላት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። 

 

 ጤና

* የምእመናን የጤና አገልግሎት ክፍል  ( FAITH COMMUNITY  NURSING PROGRAM, EVERY SUNDAY) ዘወትር እሑድ  ለምእመናን አገልግሎት ያቀርባል