ርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ከሁለተኛ ደረጃ እና ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለተመረቁ ምዕመናን ቡራኬ ከደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ አርያም ቆሞስ አባ ኃይለሚካኤል May 21, 2017  እንዲቀበሉ አደረገች። በዓይነቱ የመጀመሪያ በሆነው በዚህ ዝግጅት ላይ 26 ተመራቂዎች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን፤ ከሁለተኛ ደረጃ ጀምሮ እስከ ዶክትሬት ዲግሪ ድረስ ትምህርታቸውንን ያጠናቀቁ ምዕመናን ተገኝተውበታል። ተመራቂዎች ወደ አውደ ምሕረት እየተጠሩ ቡራኬ ሲቀበሉ የቤዛ ኲሉ ሰንበት ትምህርት ቤት ዘማርያን እና ምዕመናን "እግዚአብሔር ይመስገን ለዚህ ላደረሰን" የሚለውን መዝሙር በመዘመር ለእግዚአብሔር ምስጋናን አቅርበዋል።