በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ነዋ ሚካኤል አሐዱ እመላእክት ቀደምትትንቢተ ዳንኤል : ፲፫

በዚህ አጭር ሥነ ጽሑፍ ቆይታችን ስለ ኅዳር ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ክብረ በዓል ታሪክና በተጨማሪም ስለቤተሰባዊ ተአምር ስለተደረገልን እንነጋገራለን። ቅዱስ ሚካኤል የሚያደርገው ተአምር እልፍ አዕላፍ ቢሆንም በዚህ ዕለት ከሚታሰቡት እስራኤል ዘሥጋን ከምድረ ግብጽ እየመራ ማውጣቱን በተጨማሪም በዓለ ሢመቱን አያይዘን በመዘከር እናከብራለን። የእስራኤል ዘሥጋ ታሪክ ወደ ግብጽ መሄድ እንደምን ሆነ ብንል የዘር ረጉን ስንመለከት ጥሩ ግንዛቤ ይሰጠናል። አብርሃም ይስሐቅን ወለደ፤ ይስሐቅ ያዕቆብወለደ፤ ያዕቆብ ይሁዳንና አሥራ-አንድ ወንድሞቹን ወለደ። አስራ አንደኛው ልጅ  ዮሴፍ ይባላል።

 የዮሴፍ ወንድሞች በምቀኝነት ዮሴፍን ለእስማኤላውያን በሃያ ብር ጡት (ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ ፴፯:፲፪) ዮሴፍም በምድረ ግብጽ አሥር ዓመት በአገልግሎት አሥር ዓመት በግዞት እንደቆየ ፈርኦን ሕልም አልሞ ትርጓሜው ጠፍቶት ሳለ የዮሴፍን ዝናውን ሰምቶ ስለነበር ከግዞት አስጠርቶት ሕልሜን ተርጉምልኝ ብሎት ጠይቆት ከተረጎመለት በኋላ በክብር አፈ-ንጉሥ አድርጎ ሾሞታል። ከሰባት ዓመታት በኋላ በምድር ላይ ከባድ ረሀብ በመግባቱ የዮሴፍ ወንድሞች እህል ለመሸመት ወደ ግብጽ አገር መጡ። ዮሴፍም ወንድሞቹ መሆናቸውን ካወቀ በኋላ በመጀመሪያ ሳይነግራቸው በሁለተኛ ግን ማንነቱን ካሳወቃቸው በኋላ አበቴን አምጡልኝ ብሎ ጠየቃቸው። ያዕቆብም ዮሴፍን አውሬ በላው ብለውት ለዘመናት እያዘነ ይኖር ስለነበር የዮሴፍን መኖርና ዝና ሲሰማ ከሞት እንደተነሣለት ቆጥሮት ልጆቹንና የልጅ ልጆቹን አስከትሎ እራሱን ጨምሮ ሆነው ወደ ግብጽ ወርደው በጌሴም ተቀምጠዋል (ኦሪት ዘፀአት ምዕ )  

ከብዙ ዘመናት በኋላ የዮሴፍን ዝና ያላወቀ ፈርዖን ነገሠ። ፈርዖንን በንግሥናው ዘመን  በጣም ያሳሰበው የእስራኤል ዘሥጋ ቁጥር መብዛት ስለነበር ጠላት በነገሥታቱ ላይ ቢነሣ ተደርበው ያጠፉናል በማለት የከበደ አገዛዝ አጸናባቸው፤ ፍትህም አጎደለባቸው። እስራኤል ዘሥጋ መከራ እየተቀበሉ ፬፻፴ ዘመን ሲሰቃዩ ኖሩ። ከጊዜያት በኋላ ነብየ ሙሴ ተወለደ፤ በፈርዖን ነገሥታት አንድም አደገ። የእስራኤልን ዘሥጋ ስቃይ ከተመለከተ በኋላ ወደ ምድረ ምድያም መሸሽን መረጠ (ኦሪት ዘፀአት ምዕ. ) ነብየ ሙሴም ከኢትዮጵያው ካህን ራጉኤል ዮቶር ጋር ተገናኘ፤ ከሱ ጋርም መቀመጥን ፈቀደ። ካህኑም ልጁን ሲፓራን ለሙሴ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው ሚስቱም ሁለት ወንድ ልጅ ወለደችለት ስማቸውም ጌርሳም እና ኤሌዜር ብሎ ሰየማቸው (ኦሪት ዘፀአት ምዕ :፳፩) ጌታም ለሙሴ በአምሳለ ሐመልማል ወነበልባል ተገልጾ የሕዝቤን መካራ ፈጽሜ አይቼ ልቅሶአቸውንም ሰምቼ ላድናቸው ወረድሁ አሁንም ና! ወደ ግብጽ ልላክህ (ሐዋ : ፴፬)

አምላከ ሙሴም በፈርዖን ላይ ብዙ ተአምራትን ካደረገ በኋላ እስራኤል ዘሥጋን  ከግብጽ ባርነት ነጻ አወጣቸው። ከዚህ በኋላ ቅዱስ ሚካኤል እስራኤል ዘሥጋን  እየመራቸውና እየረዳቸው መና ከደመና እያወረደላቸው ውኃ ከጭንጫ እያፈለቀላቸው ያን እየተመገቡ ለአርባ ዘመን ተጉዘው ለምድረ ርስት ሊበቁ ችለዋል። (መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ ፲፫:፳፩) የእስራኤል ዘሥጋ ታሪክ ከፈርዖን ነጻ መውጣት የተፈጸመው ፲፭፳፰ ከክርስቶስ ልደት በፊት አካባቢ ነው። እንደ አበው አስተምህሮ ኅዳር ፲፪ ቀን ታላቁ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በኢዮር ባለችው ከተማ በሚኖሩት ኃይላት እና በአሥሩ ነገደ መላእክት ላይ አለቃ ሆኖ የተሾመበት ዕለት ነው። በተጨማሪም በዚሁ የኅዳር ወር ላይ በማግስቱ ኅዳር ፲፫ አእላፍ የመላእክት በዓል ይከበራል። አእላፍ የተባሉ መላእክት ናቸው በነገድ ዘጠና ዘጠኝ ይባሉ እንጂ ብዛታቸውን ለማወቅ አይቻልም እልፍ አዕላፍ ናቸው።

ስለ ሕዝበ እስራኤል በስደት መቆየትና ስለ ቅዱስ ሚካኤል መሪነት ይኽን ያህል ካልን ከላይ እንደገለጽነው ቤተሰባዊ ተአምር ስለተባለው ጥቂት እንበል፦ እኔና ባለቤቴ የቅዱስ ሚካኤልን ቀን በተመለከተ ዘወትር እንነጋገር ነበርበተለይ ታቦተ ሕጉ እንደ ቀድሞ በአጥቢያችን ስለሌለን ክብረ በዓልም ልናከብር አንችልም ቅዳሴም ቢሆን ሊታጎል ይችላል በማለት ያሳስበን ነበረ። ከጊዜ በኋላ ባለቤቴ ፍጹም ጥሩ ሕልም አየችና የቅዱስ ሚካኤል ታቦተ ሕጉ መጥቶ ዑደት ስናደርግ አለችኝ። እኔም በቅንነት በጊዜው የቤተ ክርስቲያናችን አለቃ መልአከ አርያም ቆሞስ አባ ሚካኤል ወደ ቅድስት አገራችን ተጉዘው ስለነበር ማንም ሳይነግረኝ ለባለቤቴ ግዴለሽም አባ ሲመጡ የቅዱስ ሚካኤል ታቦተ ሕግ ይዘው ይመጣሉ በማለት በእርግጠኝነት ነገርኳት። እንደተባለውም በቀድሞ ለጊዜያዊ በምንገለገልበት ቦታ 2315 Nicollet Ave ከቅዳሴ በኋላ መጋቤ ሃይማኖት ቀሲስ አሐዱ የቤተ ክርስቲያናችንን አለቃ መቼ እንደሚገቡ ሲያሳው አያይ በሚመጡበት  የሊቀ መላእክት ዱስ ሚካኤልን ታቦተ ሕግ ይዘው እንደሚገቡ የምሥራች ቃል አሰሙን። በዚህ ተአምር ላይ ሌላ የሚያስደንቅ ተአምር ተከስቷል ለጊዜው ይቆየን። መጋቢት ፲፪/፳፻፯  በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት የበአላት በኩር እና በዕለተ ቅዱስ ሚካኤል ታቦተ ሕጉን በአምላከ ቅዱስ ሚካኤል ፈቃድ ተቀበልን። ስለማይከፈለው ስጦታ አምላከ ቅዱስ ሚካኤልን አመስግኑ። የጽርሐ አርያም ቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት አይለየን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

ዳዊት ጌታቸው