የጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴን ዓመታዊ ክብረ በዓል የፊታችን ሐምሌ ፲፮ ቀን ፳፻፱ . (July 23, 2017) የሃገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዘካሪያስ እና ከተለያዩ ስቴቶች የተጋበዙ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን እንዲሁም ምእመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ያከበራል። 

ስለዚህም በቦታው በመገኘት የዚህ መንፈሳዊ በረከት ተሳታፊ እንድትሆኑ መንፈሳዊ ጥሪያችንን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም ስተላልፋለን።