የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በታላቅ ፍሥሐ እና ይባቤ ለማክበር የፈቀደልን ልዑል እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን። ከሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል በረከት ረድኤት ይክፈለን። እስራኤልን በመንገዳቸው የረዳቸው እኛንም ከክፉ ነገር ሁሉ በክንፎቹ ጋርዶን ይጠብቀን። ይኽንን ታላቅ በዓል ለማክበር ሁላችን ከዋዜማው ጀምረን እንድንገናኝ ቤተ ክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።