በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤዛ-ኩሉ ሰንበት ት/ቤት ተከታታይ የስድስት ወራት የሃይማኖት ትምህርት  ዘወትር ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ ከ 4:00 P.M. – 6:00 P.M. ከጥር ፳፻፱ ዓ/ም (January 2017) ጀምሮ ለመስጠት ተዘጋጅቷል። ይኽ ኮርስ በርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የስብከተ ወንጌል ክፍል እና ቤዛ-ኩሉ ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ በዓይነቱ የመጀመርያ ሲሆን ኮርሱም በደብሩ ካህናት እና በሰ/ ት/ቤት አገልጋዮች ይቀርባል፤ በኮርሱ ፍጻሜም የመመረቂያ ምስክር ወረቀት ይሰጣል። የትምህርቱ ርእሶች፦

ሀልዎተ እግዚአብሔርና ሥነ ፍጥረት፣

መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፣

የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ፣

ክብረ ቅዱሳን፣

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ፣

ሥርዓተ አምልኮ

ኮርሱን ለመውሰድ የምትፈልጉ ሁሉ በቅድሚያ መመዝገብ ስለሚኖርባችሁ ምዝገባው ዘወትር እሑድ ከቅዳሴ በኋላ እና በሰንበት ት/ቤቱ ውስጥ ስለሚደረግ በቶሎ እየመጣችሁ አነጋግሩን። ለበለጠ ማስረጃ ዓለሙ ገባ (651)442-2362 ቤካ መገርሳ (612)735-8021 አብርሃም ሰሎሞን (612) 275-9418 ደውለው ያነጋግሩ።

 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!