በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

አርብ ታኅሣሥ ፳፰/፳፻፱ ዓ/ም ከምሽቱ 5:00 P.M. ጀምሮ የልደት በዓል በካህናተ ቤተ ክርስቲያን እየተመራ በማኅሌት፣ በዝማሬ እና በቅዳሴ ይከበራል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል አምላካችን፤ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበትን ቀን ለማክበር ዝግጅቱን ሲያደርግ

የቤተ ክርስቲያኒቱ አባላት ብቻ ሳይሆኑ መላው የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች ከነቤተሰቦቻቸው መጥተው የሚያከብሩበትን ቦታ ከመልካም መስተንግዶ ጋር ለማቅረብ መቻሉንም በማረጋገጥ ነው። ሁላችንም አብረን በዓሉን ለማክበር ልዑል እግዚአብሔር ይርዳን።