ቅዳሴ፣ ማሕሌት፣ ኪዳን፣ ምህላ እና ንግሥ

* ዓመቱን በሙሉ ኪዳን ይደርሳል (6:00 A.M)

* ዘወትር እሑድ ቅዳሴ ይቀደሳል

* በሥላሴ፣ በመድኃኔዓለም፣ በማርያም፣ በሚካኤል እና በዮሐንስ ወርኃዊ በዓላት ይቀደሳል (የክርስትና ማንሳት አገልግሎት ይሰጣል)

* ጥርና ሐምሌ ሥላሴ፣ ጥቅምት እና መጋቢት መድኃኔዓለም፣

      ኅዳር እና ሰኔ ሚካኤል፣ ሰኔና መስከረም ዮሐንስ ይነግሣል

* በጾመ ፍልሰታ የሱባኤ ወቅት ሰዓታት ይቆማል፣ ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም ይተረጎማል፣ ቅዳሴ እና የሰርክ ጸሎት ይደርሳል

* በአዲስ ዓመት (በዘመን መለወጫ)፣ በልደት  በትንሣኤ እና ቤተ ክርስቲያናችን ባሏት ተጨማሪ ዐበይት በዓላት የተለያዩ መርሐ-ግብሮች ይከናወናሉ።

* በሰሞነ ሕማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሙሉ አገልግሎት ይሰጣል

ክርስትና

* ቤተ ክርስቲያናችን ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት ጀምሮ በርካታ ሕፃናት የጥምቀተ ክርስትና አገልግሎት አግኝተዋል።

ስብከተ ወንጌል እና መንፈሳዊ ትምህርት

* ዘወትር አርብ ስብከተ ወንጌል ይሰጣል

* ዘወትር ቅዳሜ መላ ምእመናንን የሚያሳትፍ የሰንበት ትምህርት ቤት መርሐ-ግብር ይደረጋል

* ዘወትር ቅዳሜ የአብነት ትምህርት እና መሠረታዊ የአማርኛ ቋንቋ ለወጣቶችና ለታዳጊ ሕፃናት ይሰጣል

* ዘወትር እሑድ ሃይማኖታዊና የሥነ-ምግባር ትምህርት ለሕፃናት እና ለወጣቶች ይሰጣል

ዕድር

* የቤተ ክርስቲያናችን አባላት የሆኑ ብቻ በአባልነት ተመዝግበው በኀዘናቸው ጊዜ መርጃ እንዲሆናቸው ታስቦ የተቋቋመው ዕድር ለአባላት አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል። 

 

 

 

 

 

 

 

 

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤዛ-ኵሉ ሰንበት ት/ቤት የተመሠረተበትን ታሪካዊ ፳ኛ ዓመታዊ በዓሉን በተለያዩ መንፈሳዊ ዝግጅቶች ከቤተ ክርስቲያናችን እና ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ተጋብዘው ከሚመጡ ካህናት ጋር በመሆን ለማክበር ተዘጋጅቷል።

 

ቦታ፡ ርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል (2601 Minnehaha Ave. Minneapolis, MN 55406)

 

መቼ፡ ከአርብ ሐምሌ ፲፭ እስከ እሑድ ሐምሌ ፲፯/፳፻፰ ዓ.ም. (July 22-24, 2016)

 

በመርሐ ግብሩ ከሚካተቱት የትምህርት፣ የመዝሙር፣ የሥነ-ጽሑፍ፣ የዐውደ ርእይ እና የመሳሰሉት በርካታ ዝግጅቶች መካከል እሑድ ሐምሌ ፲፯/፳፻፰ ዓ.ም. (July 24, 2016) "የኢዮብ መከራ እና የእግዚአብሔር ቸርነት" በሚል ርእስ የተዘጋጀ ተውኔት ይቀርባል።