-------------------

-------------------

ቤዛ-ኵሉ ሰንበት ት/ቤት

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤዛ-ኵሉ ሰንበት ት/ቤት የተመሠረተበትን ታሪካዊ ፳ኛ ዓመታዊ በዓሉን በተለያዩ መንፈሳዊ ዝግጅቶች ከቤተ ክርስቲያናችን እና ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት ተጋብዘው ከሚመጡ ካህናት ጋር በመሆን ለማክበር ተዘጋጅቷል።

ቦታ፡        ርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል (2601 Minnehaha Ave. Minneapolis, MN 55406)

መቼ፡ ከአርብ ሐምሌ ፲፭ እስከ እሑድ ሐምሌ ፲፯/፳፻፰ ዓ.ም. (July 22-24, 2016)

በመርሐ ግብሩ ከሚካተቱት የትምህርት፣ የመዝሙር፣ የሥነ-ጽሑፍ፣ የዐውደ ርእይ እና የመሳሰሉት በርካታ ዝግጅቶች መካከል እሑድ ሐምሌ ፲፯/፳፻፰ ዓ.ም. (July 24, 2016) "የኢዮብ መከራ እና የእግዚአብሔር ቸርነት" በሚል ርእስ የተዘጋጀ ተውኔት ይቀርባል።

 

 

 

 

 

የጤና እንሹራንስ (Health Insurance) ከመምረጣችን በፊት ማወቅ የሚገቡን ሦስት ጠቃሚ ነገሮች፦

1ኛ- አራቱ የ "Metal" Health ጎራዎች

       Bronze, Silver, Gold and Platinum

 

ፕላን ዓይነት

ኢንሹራንስ

ተጠቃሚ

Bronze

60%

40%

Silver

70%

30%

Gold

80%

20%

Platinum

90%

10%

2ኛ ጠቅላላ ወጪና ኢንሹራንሱ የሚሸፍነው

ምንም እንኳን የሕክምና አገልግሎት ብናደርግም ባናደርግም በየወሩ የኢንሹራንስ ክፍያ (premium) መክፈላችን የግድ ነው። ስለዚህ ከራሳችን የምንከፍለው ይኖራል ማለት ነው (You pay out-of-pocket costs, including a deductible.) ሰለዚህ በራሳችን ኢንሹራንስ ሰንገዛ ማገናዘብ ካለብን አንዱ ነው ማለት ነው።

3ኛ ፕላን እና ኔትወርክ ዓይነት (Plan and Network type)

HMO, PPO, POS, and EPO

አንዳንድ የፕላን ዓይነት በማንኛውም ዶክተር ወይም ክሊኒክ  መታየትና መጠቀምን ይፈቅዳል። አንዳንዱ ደግሞ በተወሰኑ ክሊኒኮች ቢቻ (within network) አገልግሎት ማግኘት ይፈቅዳል ወይም ክፍያው ይጨምራል። (if outside network.)

በወ/ ዘመናይ ዘሪሁን