ከተሰጡት ምርጫዎች ትክክለኛ የሆነውን ይምረጡ።

 

. ስለ ጾም ትክክል ያልሆነው የትኛው ነው?

 

ሀ) ጾም የጸሎት እናት የአርምሞ እኅት የዕንባ ምንጭና የመልካም ገድል ሁሉ ጥንተ መሠረት የሆነች የፅድቅ በር ናት

ለ) ጾም ፈቃደ አምላክ የምንፈጽምበት፤ ኃጢአታችንን ለማስተስረይ ደካማ ሥጋችንን ለነባቢት ነፍስ የምናስገዛበት ነው፤

ሐ) የዲያብሎስን ኃይል ድል መንሻ የመንግሥተ ሰማያት መውረሻ የሚሆን የሰው ልጆች ብርቱ ጥሩር ነው፤

መ) የምግብ ለውጥ ለማድረግ እና ሁልጊዜ ሥጋ መብላት ጤናችንን እንዳይጎዳ በማሰብ የምንፈጽመው ሥርዓት ነው።

 

. በዘመነ አበው፣ በዘመነ ኦሪት፣ በዘመነ ነቢያትና በዘመነ ሐዋርያት በመጾም ትልቅ በረከት ስላገኙ ሰዎች ትክክለኛውን መልስ ምረጥ!

 

ሀ) ክቡደ መዝራዕት ሊቀ ነቢያት ሙሴ በእግዚአብሔር ጣት ዓሥርቱ ቃላተ ኦሪት የተጻፈባቸውን ሁለት ጽላቶች ለመቀበል የበቃው ፵ ቀናት በመጾም ነው

ለ) ነቢዩ ኤልያስ ሞት ሳይቀምስ ወደ ብሔረ ሕያዋን በእሳት ሠረገላ ለማረግ የበቃው ፵ ቀናት ከጾመና ከጸለየ በኋላ ነው

ሐ) ነቢዩ ዳንኤል የእግዚአብሔር መልአክ የተገለጸለት ሃያ-አንድ ቀን ጾሞ ከጸለየ በኋላ ነው

መ) ሁሉም ልክ ነው።

 

፫. በጾማችን ወራት ሊኖረን የሚገቡ ምግባሮች የትኞቹ ናችው?

 

ሀ) የሠራነውን ኃጢአት በማስታወስ ራሳችንን ዝቅ አድርገን በተሰበረ መንፈስ እና በዕንባ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ

ለ) ወደ ነፍስ አባታችን ቀርበን ንሰሐችንን በማቅረብ እና እርስ በእርሳችንም ይቅር መባባል

ሐ) የታመሙ እና የታሰሩትን በመጎብኘት፣ እንዲሁም  ለድኆችና ለተጨነቁት ካለን መብልና ሀብት ማካፈል

መ) ሁሉም ልክ ነው።

 

፬. ዓብይ ጾምን ለምን እንጾማለን?

 

ሀ) ሙሴ በሲና ተራራ ፵ ቀንና ፵አርባ ሌሊት እንደቆየ ለማስታወስ፤

ለ) ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ ቆሮንቶስ ፵ ቀንና ፵ ሌሊት በመጾም ለእኛ ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የጾመው ጾም በመሆኑ፤

ሐ) ኤልያስ እስከ እግዚአብሔር ተራራ እስከ ኮሬብ ድረስ ፵ ቀንና ፵ ሌሊት መሄዱን ለማስታወስ፤

መ) ዔሊ በእስራኤል ላይ ፈራጅ የነበረበትን ፵ ዓመታት ለማስታወስ፤

ሠ) ሁሉም ልክ ነው።

 

፭. ለዓብይ ጾማችን መነሻ የሆነንን ምክንያት የምናገኝበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የትኛው ነው?

 

ሀ) ማቴዎስ ፬:፩-፪              ለ) ማርቆስ ፩፡፩-፪-፲፫   

ሐ) ሉቃስ ፬፡፩-፪               መ) ሁሉም ልክ ነው።

 

፮. የጾማችን የመጀመሪያ ሣምንት ምን ይባላል?

ሀ) መጻጉዕ             ለ) ምኩራብ           ሐ) ዘወረደ     መ) ሆሣዕና

 

፯. የጾማችን ስምንተኛ ሣምንት ምን ይባላል?

ሀ) መጻጉዕ          ለ) ምኵራብ      ሐ) ዘወረደ      መ) ሆሣዕና

 

፰. ጌታችን ዓብይ ጾምን አርባ ቀንና አርባ ሌሊት እንደጾመው ስናውቅ እኛ ግን ለምን 55 ቀናት እንጾማለን?


ሀ)
  የአቆጣጠር ስሕተት ነው፤   

ለ) በጾማችን ወቅት ያሉት ሰባት ረቡዕ እና ስምንት ዓርቦች ስለማይቆጠሩ፤    

ሐ) የመጀመርያው ሳምንት ጾመ ሕርቃል፤ የመጨረሻው ሳምንት ደግሞ ሰሙነ ሕማማት ተብሎ ስለሚጾም ነዉ።

መ) ለምን እንደሆነ አይታወቅም።

 

፱. በመጽሐፍ ቅዱሳችን እንደተገለጸው ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሌላ ፵ ቀን እና ፵ ሌሊት የጾሙ ሁለት ሰዎች እነማን ናቸው?

ሀ) ሙሴ እና ኤልያስ፤             ለ) ሙሴ እና ዮሴፍ፤    

ሐ) ዮሴፍ እና ኤልያስ፤             መ) ዳንኤል እና ኤልያስ፤

 

፲. የዐቢይ ጾማችን ሰባተኛ ሣምንት በስሙ የተሠየመለት ኒቆዲሞስን አስመልክቶ ትክክል ያልሆነው የትኛው ነው

 

ሀ) ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ ነገር ግን ጌታችንን እስከ መጨረሻ የተከተለ ከ፲፪ቱ ሐዋርያት አንዱ ነው፤

ለ) ፈሪሳዊ እና በሮማውያን የተሾመ የአይሁድ አለቃ ባለ ሥልጣን የነበረ ሰው ነው፤

ሐ) አለቅነትን ከመምህርነት ዕውቀትን ከትህትና ምሁርነትን ከደፋርነት አስተባብሮ የያዘ የጌታችን የምሽት ተማሪ የነበረ ሰው ነው፤

መ) የክርስቶስን ሥጋ ከአለቆች ለምኖ የገነዘ እና በአዲስ መቃብርም     ያሳረፈ ሰው ነው።

 

መልሶችን ለማየት እዚህ ይጫኑ

በዶ/ ሰሎሞን ፎሌ