Print

ከብሉይ ኪዳን እና ከሐዲስ ኪዳን ተውጣጥተው የቀረቡ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎች ናቸውና እያንዳንዱን ጥያቄ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር በማስተያየት ለመመለስ እንሞክር።

፩)  እርሱ ሊልቅ እኔ ግን ላንስ ያስፈልጋል።” በማለት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረው ማነው?

ሀ) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ                     

ለ) ወንጌላዊው ዮሐንስ

ሐ) ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ                     

መ) መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ

 

፪) የአብርሃም ስም አብራም፤ የሣራ ስም ሦራ፤ የቅዱስ ጳውሎስ ስም ሳውል ተብሎ እንደሚታወቀው ሁሉ የቅዱስ ጴጥሮስ ስም ማን በመባል ይታወቅ ነበር?

ሀ) ኬፋ

ለ) ዴማስ

ሐ) ስምዖን

መ) ዲዲሞስ

 

፫) ፊልጶስ ሳይጠራህ ከበለስ በታች ሳለህ አየሁህ” በማለት ጌታ ያናገረው ማንን ነው?

ሀ) እንድርያስን

ለ) ዘብዴዎስን

ሐ) ያዕቆብን

መ) ናትናኤልን

 

፬)  ጌታ ሆይ መቅጃ የለህም ጕድጓዱም ጥልቅ ነው፤ እንግዲህ የሕይወት ውኃ ከወዴት ታገኛለህ? በማለት ጌታን ያነጋገረችው ሴት ማን ነች?

ሀ) ራሔል

ለ) የማርቆስ እናት ማርያም

ሐ) መግደላዊት ማርያም

መ) ሳምራዊቷ

 

፭) ከሠላሳ ስምንት ዓመት ጀምሮ ታምሞ የነበረው ሰው የተፈወሰው ቤተ ሳይዳ በመባል በምትታወቀው መጠመቂያ ተጠምቆ ነው። እውነት ወይስ ሐሰት?

 

፮) ጌታ በአምስት የገብስ እንጀራና በሁለት ዓሣ አምስት ሺህ ሰዎችን በመገበበት ወቅት “እያንዳንዳቸው ትንሽ ትንሽ እንኳ እንዲቀበሉ የሁለት መቶ ዲናር እንጀራ አይበቃቸውም” በማለት ጌታን ያናገረው ማነው?

ሀ) ፊልጶስ

ለ) ዮሐንስ ወልደ ዘብዴዎስ

ሐ) ናትናኤል

መ) ስምዖን ጴጥሮስ

 

 

፯) በትንሣኤ ሙታን የማያምኑት እነማን ናቸው?

ሀ)        ፈሪሳውያን                    

ለ)        ሰዱቃውያን

ሐ)        ቆሮንቶሳውያን                

መ)       ሁሉም

 

፰) ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ መሬት እንትፍ ብሎ በምራቁም ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዕውሩን ዓይኖች ቀብቶ ሂድና ታጠብ ብሎ የላከው ከየትኛው መጠመቂያ ነው?

ሀ) በቤተ ሳይዳ

ለ) በዮርዳኖስ

ሐ) በሰሊሆም

መ) በገሊላ

 

፱) አልዓዛርን ከእንቅልፉ ላስነሣው እሄዳለሁ በማለት ጌታ ወደ ቢታንያ ለመሄድ ሲነሣ ይገድሉታል በማለት አስቦ ደቀ መዛሙርቱን “ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛ ደግሞ እንሂድ” በማለት የተናገረው ማነው?

ሀ) ዲዲሞስ የሚሉት ቶማስ

ለ) ስምዖን የተባለው ጴጥሮስ

ሐ) የቀሬናው ስምዖን

መ) የአስቆሮቱ ይሁዳ

 

፲) አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ” ያለው አረጋዊው ስምዖን “በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል” ብሎ የተናገራት ማንን ነው?

ሀ) ቅድስት ኤልሳቤጥን

ለ) ቅድስት ሐናን

ሐ) ቅድስት ድንግል ማርያምን

መ) መግደላዊት ማርያምን

 

፲፩) ከአሥራ-ሁለቱ ሐዋርያት መካከል አንደኛው ሉቃስ ነው። እውነት ወይስ ሐሰት

 

፲፪) እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” በማለት ትንቢት የተናገረው ነቢዩ ኤርምያስ ነው። እውነት ወይስ ሐሰት

 

፲፫) ቁራዎች ጠዋትና ማታ እንጀራና ሥጋ ያመጡለት የነበረውና በሰራፕታ ምድር አንዲት ሴት ትመግበው የነበረው ነቢይ ማን ነው?

ሀ) አብርሃም

ለ) ሙሴ

ሐ) ኤልያስ

መ) ያዕቆብ

 

 

በአቶ አብርሃም ሰሎሞን