Print

፩- በገሊላ ባሕር አጠገብ አሳ በማጥመድ ላይ ሳለ የተጠራው፦

ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ 

ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ     

ሐ) ሁለቱም

፪- ጌታችን ስለ ምን ታሳድደኛለህ በማለት ከክፉ ሥራው ላይ ለአገልግሎት የመረጠው ሐዋርያ ማነው?

ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ 

ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ     

ሐ) ሁለቱም

 ፫-  ጌታችን አስቀድሞ ከመረጣቸው ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት መካከል እንደ አንዱ ሆኖ የሚቆጠረው የትኛው ሐዋርያ ነው?

ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ

ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ

ሐ) ሁለቱም

፬- ሕግን ጠንቅቆ የተማረና በጋብቻ ሕይወት ውስጥ ያልኖረ፦

ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ

ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ

ሐ) ሁለቱም

፭- መጽሐፍን የማያውቅና ያልተማረ ተብሎ የተነገረለት ሐዋርያ ማነው? 

ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ

ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ

ሐ) ሁለቱም

፮- ለተገረዙት የሆነው የወንጌል አደራ የተሰጠው ለየትኛው ሐዋርያ ነው?

ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ

ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ

ሐ) ሁለቱም

፯- ላልተገረዙት ወይም ለአሕዛብ የወንጌል አደራ የተሰጠው፦

ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ

ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ

ሐ) ሁለቱም

፰- በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። የመንግሥተ ሰማያትንም መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ፤ በምድር የምታስረው ሁሉ በሰማያት የታሰረ ይሆናል፥ በምድርም የምትፈታው ሁሉ በሰማያት የተፈታ ይሆናል። ተብሎ በጌታ የተነገረለት፦

ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ

ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ

ሐ) ሁለቱም

፱- የእኔን እግር ለዘላለም አታጥብም በማለት ለጌታ የመለሰና በኋላም እግሬን ብቻ ሳይሆን እጄንና እራሴንም እጠበኝ ያለው ሐዋርያ ማነው?

ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ

ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ

ሐ) ሁለቱም

፲- መንፈስ ቅዱስን የመስጠት ኃይልና ድንቅና ተአምራት በማድረግ የታወቀው ሐዋርያ ማን ይባላል?

ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ

ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ

ሐ) ሁለቱም

፲፩- ሙታንን ያሥነሣና ስሙም በጌታ የተቀየረለት ሐዋርያ ማነው?

ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ

ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ

ሐ) ሁለቱም  

፲፪- በደለኞችን በመቅጣትና የወንጌልን ቃል ለማስተማር ብርቱና ደፋር የነበረ ሐዋርያ ማነው?

ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ 

ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ

ሐ) ሁለቱም

፲፫- እጅግ በጣም ትሁትና ለብዙ ስደትና ፈተና የተጋለጠ ሐዋርያ፦

ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ 

ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ  

ሐ) ሁለቱም

፲፬- አይሁድ አንድ ሲጎድል አርባ ግርፋት አምስት ጊዜ ገረፉኝ። ሦስት ጊዜ በበትር ተመታሁ፤... ብዙ ጊዜ በመንገድ ሄድሁ፤ በወንዝ ፍርሃት፥ በወንበዴዎች ፍርሃት፥ በወገኔ በኩል ፍርሃት፥ ... ነበረብኝ፤ ... በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርሁ። የቀረውንም ነገር ሳልቆጥር፥ ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው። በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረበት መልእክት ምዕራፍና ቁጥር፦

ሀ) ፩ቆሮ.፲፩፡፳፩-፳፰

ለ)  ፩ቆሮ.፳፩፡፳፩-፳፰

ሐ) ፪ቆሮ.፳፰፡፳፩-፳፰

መ)  ፪ቆሮ.፲፩፡፳፩-፳፰

፲፭- የሰማዕትነትን አክሊል የተቀዳጀና ክብረ በዓሉም በሐምሌ ፭ ቀን የሚከበርለት ሐዋርያ ማን ይባላል?

ሀ) ቅዱስ ጳውሎስ

ለ) ቅዱስ ጴጥሮስ

ሐ) ሁለቱም 

፲፮- ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቀደመ ስሙ ማን ተብሎ ይታወቃል? ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስስ?_________________________________________________________

፲፰- በአንድ ጊዜ ሦስት ሺህ ሰዎች በትምህርቱ አምነው የተጠመቁለት ሐዋርያ ማነው? _______________________________________________________

፲፱- ቁልቁል ተሰቅሎ ሕይወቱን ያጣው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲሆን አንገቱ በሰይፍ ተቆርጦ ሕይወቱን ያጣው ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ነው። እውነት/ ሐሰት

፳- የመውጊያውን ብረት ብትቃወም በአንተ ይብስብሃል በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን የተናገረው ማነው?______________________________________________

 

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።

አብርሃም ሰሎሞን