የቅዱስ ሉቃስ ወንጌል ጥናት በጥያቄ መልኩ (ከምእራፍ ፱ እስከ ፲፮)

የመጀመርያው ሁለት ጥያቄዎች ከምእራፍ ፱ ቀጣዩ ሁለት ጥያቄዎች ከምእራፍ ፲ እያለ ይቀጥላል።

)   ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ጌታ ሆይ፥ ኤልያስ ደግሞ እንዳደረገ እሳት ከሰማይ ወርዶ ያጥፋቸው እንል ዘንድ ትወዳለህን? ያሉት እነማን ናቸው?

፪)   ለቀበሮዎች ጕድጓድ ለሰማይም ወፎች መሳፈሪያ አላቸው፥ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም በማለት የተናገረው ማነው?

፫)   ጌታችን በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው በአመድም ተቀምጠው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበር በማለት የወቀሳቸው ከተሞች እነማን ናቸው?

፬)   በወንበዴዎች እጅ ተደብድቦ ለወደቀው ሰው ቁስሉ ላይ ዘይት በማፍሰስ እና ከወደቀበት አንሥቶ በመንከባከብ መልካም ያደረገለት ማነው?

፭)   ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ ጸሎት እንዳስተማረ ከነቢያት መካከል ለተከተሉት ደቀ መዛሙርት ጸሎት ያስተማረ ማነው?

፮)   ፍርድንና እግዚአብሔርን መውደድ ስለምትተላለፉ፥ በምኵራብም የከበሬታ ወንበር በገበያም ሰላምታ ስለምትወዱ፥ ወዮላችሁ በማለት ጌታችን የተናገረው ማንን ነው?\

፯)   ጌታችን ደቀ መዛሙርቱን ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠበቁ ብሏቸዋል። የፈሪሳውያን እርሾ የተባለው ምንድን ነው?

፰)   ጌታችን በሰው ፊት የሚመሰክርልኝ በማን ፊት  ይመሰክርለታል? በሰውስ ፊት የሚክደኝ በማን ፊት ይካዳል? አለ?

፱)   ኢየሱስ ክርስቶስ ቀበሮ ያለው ማንን ነው?

፲)   ጌታችን ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ፥ እናንተም አልወደዳችሁም በማለት የተናገረው ማንን ነው?

፲፩)  ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናንተ አህያው ወይስ በሬው በጕድጓድ ቢወድቅ በሰንበት ወዲያው የማያወጣው ማን ነው? በማለት ስለ ምን አስተማረ?

፲፪)  ኢየሱስ ክርስቶስ ይኽን በማድረግህ በጻድቃን ትንሣኤ ይመለስልሃል በማለት የተናገረው ማንን ነው? ስለ ምንስ ነው?

፲፫)  ጌታችንን ይህስ ኃጢአተኞችን ይቀበላል ከእነርሱም ጋር ይበላል ብለው እርስ በርሳቸው ያንጎራጎሩት እነማን ናቸው?

፲፬)  በሉቃስ ወንጌል ምእራፍ ፲፭ ላይ ጠፍተው የተገኙ ምንና ምን ናቸው?

፲፭)  ሁለት ጌቶች ተብለው የተጠቀሱት ማንና ማን ናቸው?

፲፮)  በአብርሃም እቅፍ ተቀምጦ የታየው ሰው ማን በመባል ይታወቃል?

 

አብርሃም ሰሎሞን