የዚህ ወር የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጥያቄዎቻችንን ለመመለስ የቅዱስ ማርቆስን ወንጌል ማጥናት ያስፈልግዎታል። የማርቆስ ወንጌል አሥራ ስድስት ምዕራፎች ስላሉት አሥራ ስድስቱም ጥያቄዎች የወጡት በቅደም ተከተል ከምዕራፍ አንድ ጀምሮ እስከ አሥራ ስድስት ካሉት ምዕራፎች ነው። ቁጥር አንድ ጥያቄ ከምዕራፍ አንድ ቁጥር ሁለት ጥያቄ ከምዕራፍ ሁለት ቁጥር ሦስት ጥያቄ ከምዕራፍ ሦስት እያለ እስከ አሥራ ስድስት ምዕራፍ ድረስ ይቀጥላል በመሆኑም ጥያቄውን ለመመለስ አሥራ ስድስቱንም ምዕራፍ ለመቃኘት ያስችላችኋል ተብሎ የተዘጋጀ ነው።

 

፩) የጌታን መንገድ አዘጋጁ ጥርጊያውንም አቅኑ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ ተብሎ በነቢዩ በኢሳይያስ የተነገረለት ነቢይ ማነው?

 

፪) ኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊጦሙ ይችላሉን? ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊጦሙ አይችሉም። ሲል ስለማን ተናገረ?

 

፫) ለሰው ልጆች ኃጢአት ሁሉ የሚሳደቡትም ስድብ ሁሉ ይሰረይላቸዋል፤ በመንፈስ ቅዱስ ላይ የሚሳደብ ሁሉ ግን የዘላለም ኃጢአት ዕዳ ይሆንበታል እንጂ ለዘላለም አይሰረይለትም። በማለት የተናገረው ማነው?

 

፬) ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቷችኋል የተባሉት እነማን ናቸው?

 

፭) ጌታችን ሞታ የነበረችውን ጣሊታን ወደ ምኵራቡ አለቃ ቤት በመሄድ ሲያድናት ከጌታ ጋር አብረው የሄዱት ሐዋርያት እነማን ነበሩ?

 

፮) ሐዋርያት እየፈወሱና ንስሐ ግቡ እያሉ ሲሰብኩ መጥምቁ ዮሐንስ ከሙታን ተነሥቶአል ስለዚህም ኃይል በእርሱ ይደረጋል ያለው ማነው?

 

፯) ከሰው የሚወጣው ሰውን የሚያረክስ ነው እያለ ጌታ ሲያስተምር ከሰው የሚወጡት ነገሮች ምንድን ናቸው?

 

፰) ጌታችን ወደ ኋላዬ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን ነገር አታስብምና ያለው ምንን ነው?

 

፱) ጌታችን በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱ በተገለጠበት ጊዜ በተራራው ላይ የተገኙት አምስቱ እነማን ነበሩ?

 

፲) በክብርህ ጊዜ አንዳችን በቀኝ አንዳችንም በግራህ መቀመጥን ስጠን ብለው ጌታን የጠየቁት የዘብዴዎስ ልጆች እነማን ናቸው?

 

፲፩) ጌታችን ለጸሎት ከመቆማችን በፊት ምን ማድረግ እንደሚገባን ነው የነገረን?

 

፲፪) ትንሣኤ ሙታን የለም በማለት የሚታወቁት የምን ወገኖች ናቸው?

 

፲፫) ጌታችን በመቅደስ ትይዩ በደብረ ዘይት ተቀምጦ ሳለ ድንጋይ በድንጋይ ላይ ሳይፈርስ በዚህ አይቀርም ብሎ በመናገሩ ይህ መቼ ይሆናል፤ ምልክቱስ ምንድር ነው? በማለት የጠየቁት እነማን ናቸው?

 

፲፬) የቡሩክ ልጅ ክርስቶስ አንተ ነህን? በማለት ጌታችንን የጠየቀው ማነው?

 

፲፭) ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሰቀል ሲፈረድበት ምሕረት የተሰጠውና ከእስር የተፈታው ነፍሰ ገዳይ ማን ይባላል?

 

፲፮) ጌታ ሰባት አጋንንት ያወጣላት ሴት ማን ትባላለች?

 

  ዶ/ር ሰሎሞን ፎሌ 

 

 መልሶችን ለማየት እዚህ ይጫኑ