የአብነት ትምህርት ቤት እርዳታ ፕሮጀክት ማመልከቻ

Request for Proposal የአብነት ትምህርት ቤት እርዳታ ፕሮጀክት ማመልከቻ እዝህ ይጫኑ!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል (Minneapolis, MN)

የቤተ ክርስቲያናችን የምግባረ ሠናይ(በጎ አድራጎት)እና ጤና አገልግሎት ክፍል በ ፳፻፲፮ ዓ.ም. ባስያዘው እቅድ መሰረት የአብነት ትምህርት ቤቶችን ለመርዳት የ$2ሺ ዶላር በጀት በአጠቃላይ ጉባኤ መፈቀዱ ይታወሳል። ይህንን እቅድ ለመተግበር እንዲያስችል ምዕመናን እና ካህናት የተሟላ ሀሳብ/ፕሮጀክት (project proposal) እንዲያቀርቡ ክፍሉ በትህትና ይጠይቃል።

ክፍሉ ፕሮጀችት ማመልከቻዎችን ከሰበሰበ በኋላ፦
1. የቤተ ክርስቲያናችንን ራዕይ የሚያሟላውን (25%)፣
2. በስራ የሚውለውን ገንዘብ ተከታትሎ ሪፖርት ማድረግ የሚችል የአስፈጻሚ ብቃት ያለውን(25%)፣
3. ሰፊ ተደራሽነት ያለውን(25%) እና
4. የሚቀርፈውን ችግር እና ለአስተዳደር የሚውለውን የገንዘብ መጠን (25%) ግምት ውስጥ በማስገባት በኮሚቴ ተገምግሞ እና በሰበካ ጉባኤው ውሳኔ የተመደበውን በጀት ለተመረጠው ፕሮጀክት ያውላል።

በዚህም መሰረት ፕሮጀክት እንዲያቀርቡ እየጠየቅን፤ የሚከተሉትን ጥያቄዎች በቀጥታ የሚመልስ የተሟላ ማመልከቻ ከJanuary 22, 2024 (እኤአ) 11:59am በፊት በዚህ ቅጽ እንዲያቀቡ በትህትና እንጠይቃለን።