መዝሙር (በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ) April 14, 2024 (First Mezmur)

በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ
==============
 በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ (4)
 ጨነቀኝ ጠበበኝ ነፍስየ ወዲያልኝ (2)

ተሸክሜ የኃጢአት ክምር (2)
ይመሻል ይነጋል በከንቱ ሰዞር (2)
ገሰገሰ ቀኑ ጨለመብኝ (2)
ዋ ለነፍሴ ምንም ስንቅ አልያዝኩኝ (2)

 በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ (4)
 ጨነቀኝ ጠበበኝ ነፍስየ ወዲያልኝ (2)

በድያለሁ ወዳንተ እጮሃለሁ
ይቅር በለኝ እማፀንሃለሁ
ችላ አትበለኝ ከፊትህ ቆሜአለሁ (2)

 በሥራዬ የት ይሆን መግቢያዬ (4)
 ጨነቀኝ ጠበበኝ ነፍስየ ወዲያልኝ (2)

አለፈብኝ በከንቱ ጊዜዬ (2)
እየጓጓሁ ለዚች ለሥጋዬ (2)
በንስሐ ሳላጥበው እድኔን (4)
ልትደርስ ነው ያች ፈተና ቀን (2)