የልደት ማታ መዝሙር (እናምናለን) January 6, 2018


ሐዋርያት አበው እንዳስተማሩን
ስለ ሰው ልጅ ድኅነት አምላክ ሰው መሆኑን
በስሙ የተጠራን እኛ እናምናለን
መለኮት ከሥጋ ተዋሕዷል ብለን

እናምናለን እኛ ሁለት ልደታትን
የአብ ልጅ ከድንግል ዳግም መወለዱን(2)

ስግደት የሚገባው የአብ አካላዊ ቃል
ከክቡር ዙፋኑ ከሦስትነት ሳይጎድል
በዚህ ዓለም መጥቶ ሰው ሆኗል ከድንግል
ከአብ አንድነቱ ከቶም ሳይከፈል

እናምናለን እኛ ሁለት ልደታትን
የአብ ልጅ ከድንግል ዳግም መወለዱን(2)

ቃልም ሥጋ ሆኖ በእኛ ላይ አድሮ
ወልደ አብ ወልደ ማርያም በተዋሕዶ ከብሮ
ፍጹም የአምላክ ልጅ ፍጹም ሰውነቱ
ተገልጧል በድንግል በዳግም ልደቱ

እናምናለን እኛ ሁለት ልደታትን
የአብ ልጅ ከድንግል ዳግም መወለዱን(2)