መዝሙር (ምን ሰማህ ዮሐንስ) December 9, 2018
ምን ሰማህ ዮሐንስ በማህጸን ሳለህ (፪)
ህፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ (፪)
እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ (፪)
ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ (፪)
ከተፈጥሮ በላይ ያሰገደህ ክብር
እንዴት ቢገባህ ነው የእናታችን ፍቅር (፪)
ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ
ለውጦኛልና የሰላምታ ቃሏ (፪)
ምን ሰማህ ዮሐንስ በማህጸን ሳለህ (፪)
ህፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ (፪)
እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ (፪)
ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ (፪)
በረሀ ያስገባህ ለብዙ ዘመናት
ምን ያለ ራዕይ እንዴት ያለ ብሥራት (፪)
አንደ አዲስ ምስጋና ስልቱ የተዋበ
ተደምጦ የማያውቅ ጭራሽ ያልታሰበ (፪)
ምን ሰማህ ዮሐንስ በማህጸን ሳለህ (፪)
ህፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ (፪)
እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ (፪)
ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ (፪)
ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም
ድንግል ስለሆነ በህይወቱ ፍፁም (፪)
ከማህፀን ሳለ ተመርጦ በጌታ
ለማዳመጥ በቃ የኪዳን ሰላምታ (፪)
ምን ሰማህ ዮሐንስ በማህጸን ሳለህ (፪)
ህፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ (፪)
እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ (፪)
ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ (፪)