መዝሙር (ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ) December 23, 2023 (Second Mezmur)

ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
==============
 ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
 በአካለ ስጋ ዕና በአካለ ነብስ
 በአካለ ነብስ ያሉ
 ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ

የእግዚአብሔር አይኖቹ ጻድቃንን ከማየት
ጆሮቹም አይርቁም እነሱን ከመስማት
የጻድቅ ሰው ጸሎት ኃይልን ታደረጋለች
በምልጃቸው እንመን አናመታ በአንዳች

 ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
 በአካለ ስጋ ዕና በአካለ ነብስ
 በአካለ ነብስ ያሉ
 ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ

ኃጥኡ ነዌ እንኩአን በሰከኦል እያለ
ስለ ወንድሞቹ ምህት ከለመነ
እናተማ ጻድቃን በገነት ያላችሁ
ምንኛ ትረዱን አምነን ስንጠራችሁ

 ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
 በአካለ ስጋ ዕና በአካለ ነብስ
 በአካለ ነብስ ያሉ
 ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ

ጊዜያዊ መከራ ሳያሰቃያቸው
እሳት ዕና ስለት ሳያስፈራራቸው
ሰማያዊይ ተስፋ ስለሚታያቸው
በመከራው ሁሉ ጸኑ በዕምነታቸው

 ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
 በአካለ ስጋ ዕና በአካለ ነብስ
 በአካለ ነብስ ያሉ
 ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ

ቀዝቃዛ ውሃ ዐደንኳን በፃድቅ ሰው ስም
የሚያጠጣ በኖር ዋጋው አይጠፋም
ብሎ እንዳስተማር ጌታ በወንጌሉ
አምነን እንፈፅመው ዋጋ ያሰጣሉ

 ጻድቃን ሰማዕታት በሙሉ
 በአካለ ስጋ ዕና በአካለ ነብስ
 በአካለ ነብስ ያሉ
 ከፈጣሪ አማልደው እኛን ያስምራሉ