መዝሙር (ስምህ በሁሉ ተመሰገነ) February 4, 2024 (First Mezmur)

ስምህ በሁሉ ተመሰገነ
==============
 ስምህ በሁሉ ተመሰገነ
 ከክብር በላይ ክብርህ ገነነ
 አንተን ማወደስ ያስደስተናል
 ስምህን ማክበር ክብራችን ሆኖአል /2/

አምላክ ተመስገን በሰማያት
ስምህ ይወደስ በፍጥረታት
ከህፃናት አፍ ምስጋና ይውጣ
አንተን ማመስገን ይሁን የኛ ዕጣ /2/

 ስምህ በሁሉ ተመሰገነ
 ከክብር በላይ ክብርህ ገነነ
 አንተን ማወደስ ያስደስተናል
 ስምህን ማክበር ክብራችን ሆኖአል /2/

በምግብ እጦት ብንሰቃይም
ማህሌትህን አናቁአርጥም
የመከራ ዶፍ ቢወርድብንም
እንዘምራለን ለአምላካችን ስም /2/

 ስምህ በሁሉ ተመሰገነ
 ከክብር በላይ ክብርህ ገነነ
 አንተን ማወደስ ያስደስተናል
 ስምህን ማክበር ክብራችን ሆኖአል /2/

ሰማዩ ዝናብ ደመና ቢያጣ
ፍቅርህ በእኛ ውስጥ አላቁአረጠም
ቸርነትህን እንጠብቃለን
ከአንተ ደጅ አምላክ የት እንሄዳለን /2/

 ስምህ በሁሉ ተመሰገነ
 ከክብር በላይ ክብርህ ገነነ
 አንተን ማወደስ ያስደስተናል
 ስምህን ማክበር ክብራችን ሆኖአል /2/