Ebola Factsheet ስለኢቦላ ግንዛቤ

ኢቦላ በሽታ



እስካሁን ተለይተው የታወቁ አምስት ዓይነት የኢቦላ ቫይረስ ዝርያዎች ያሉ ሲሆን ከነዚህ መካከል አራቱ በሰው ላይ በሽታን መፍጠር ችለዋል። ስማቸውም፦ Zaire ebolavirus; (የዛየር ኢቦላ ቫይረስ)፣ Sudan ebolavirus; (የሱዳን ኢቦላ ቫይረስ) Tai Forest ebolavirus, (የታይላንድ ጫካ ኢቦላ ቫይረስ፣ Cote d'ivoire ebolavirus; (ከዚህ ቀደም ኮትዲቩዋር ትባል የነበረችው ሃገር ኢቦላ ቫይረስ) እና Bundibugyo ebolavirus (ቡንዲቡግዮ ኢቦላ ቫይረስ) ናቸው። አምስተኛው Reston ebolavirus (ሬስቶን ኢቦላ ቫይረስ) የሚባለው በዝንጀሮ ዝርያዎች ላይ ብቻ እንጂ በሰው ላይ እስካሁን በሽታ አላመጣም።
ኢቦላ በበርካታ የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ ይገኛል። የመጀመሪያው የኢቦላ ዝርያ እ.ኤ.አ በ1976 አሁን ዲሞክራቲክ ሪፖብሊክ ኦፍ ኮንጎ ተብላ በምትጠራው ሃገር ውስጥ ኢቦላ ወንዝ አጠገብ ተገኘ። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ፣ አልፎ አልፎ በተዘበራረቀ መልኩ አፍሪካ ውስጥ በርካታ ወረርሽኞች ተነስተው ነበር።
የኢቦላ የተፈጥሮ ምንጭና አስተናጋጁ ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም። ሆኖም ግን፣ ባሉት ተጨባጭ መረጃዎች ላይ እና ተመሳሳይ ባሕሪ ካላቸው ቫይረሶች ተፈጥሮ በመነሳት፣ ተመራማሪዎች እንሰሳ ወለድ እንደሆነ እና ዋንኛ ምንጩ ደግሞ የለሊት ወፎች እንደሆኑ ያምናሉ። ከአምስቱ ንዑሳን የቫይረሱ ዓይነቶች አራቱ በአፍሪካ ውስጥ በሚገኙ እንስሳት ላይ ብቻ የሚገኙ ናቸው።

መተላለፊያ መንገድ

ዋንኛው የኢቦላ የተፈጥሮ ምንጭና አስተናጋጁ ምን እንደሆነ ስላልታወቀ፣ በሽታው እንደ ወረርሺኝ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ላይ እንዴት ሊከሰት እንደቻለ ሊታወቅ አልቻለም። ሆኖም ግን፣ ተመራማሪዎች የመጀመሪያው በሽተኛ በበሽታው ሊጠቃ የቻለው በበሽታው ከተጠቃ እንስሳ ጋር በነበረው ንክኪ እንደሆነ ያምናሉ። በሰው ልጅ ላይ በሽታው ሲከሰት፣ ወደ ሌሎች ቫይረሱ ሊሰራጭባቸው የሚችልባቸው በርካታ መንገዶች አሉ። ከነዚህ መንገዶች መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፦
• በኢቦላ በሽታ ከተያዘ ሰው ደም ወይም (ሠገራን፣ ምራቅን፣ ሽንትን፣ ትውከትን እና የወንድ የዘር ፈሳሽን ጨምሮ ነገር ግን በነዚህ ሳይወሰን) የሰውነት ፈሳሽ ጋር ቀጥታ ንክኪ ማድረግ
• (እንደ መርፌ እና ሲሪንጆች የመሳሰሉ) በበሽታው በተጠቃ ግለሰብ ወይም በበሽታው በተጠቃ እንስሳ የተበከሉ ዕቃዎች ጋር ንክኪ ማድረግ
በደም ውስጥ ወይም በሰውነት ፈሳሽ ውስጥ ያለው ቫይረስ ወደ ሌላ ሰው ሰውነት በቆሰለ ቆዳ ወይም በስስ ብልቶች ለምሳሌ በዓይን፣ በአፍንጫ፣ ወይም በአፍ በኩል ሊገባ ይችላል። ቤተሰቦች እና ጓደኞች የታመሙባቸውን ሰዎች በሚያስታምሙበት ወቅት ቅርብ ንክኪ ስለሚኖራቸው በቤተሰቦች እና በጓደኞች መካከል ኢቦላ በሽታን አምጪ ቫይረሶቹ ብዙውን ጊዜ ይሰራጫሉ።
Please click below to read more!