መዝሙር (ነፍሴ ሆይ) March 4, 2018


 ነፍሴ ሆይ (፪)
 እግዚአብሔርን በቅን አገልግይ (፪)

የተቀበለው በቀራንዮ ያን ሁሉ መከራ በመስቀሉ ላይ
ላንቺ ሲል ነውና ነፍሴ ሆይ

 ነፍሴ ሆይ (፪)
 እግዚአብሔርን በቅን አገልግይ (፪)

ተዘጋጅተሽ ኑር ሁል ጊዜ
በነገ በዛሬ እንዳትታለይ (፪) ነፍሴ ሆይ

 ነፍሴ ሆይ (፪)
 እግዚአብሔርን በቅን አገልግይ (፪)

በንስሀ ጥምቀት ታጠቢና
ክቡር ደሙን ጠጪ ስጋውንም ብይ (፪) ነፍሴ ሆይ

 ነፍሴ ሆይ (፪)
 እግዚአብሔርን በቅን አገልግይ (፪)

ዘላለም በደስታ እንድትኖሪ
ከዘላለም ቤትሽ መንግስተ ሰማይ (፪)ነፍሴ ሆይ