መዝሙር (እውነት ስለሆነ) March 18, 2018

< >


 እውነት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ
 ዋለ በአደባባይ ሲሰደብ ሲከሰስ
 የሐሰት ዳኝነት አምላክን ወቀሰው
 ህይወት ሰጠን እንጂ ጥፋቱ ምንድን ነው

ከቃሉ እብለትን ባያኙበትም
ዝምታውን አይተው አላዘኑለትም
ባላወቁት መጠን ጠሉት ካለበደል
ጥፋቱ ምን ይሆን የሚያደርስ ከመስቀል(፪)

 እውነት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ
 ዋለ በአደባባይ ሲሰደብ ሲከሰስ
 የሐሰት ዳኝነት አምላክን ወቀሰው
 ህይወት ሰጠን እንጂ ጥፋቱ ምንድን ነው

የልቡን ትህትና ፍቅሩን ሳያስተውሉት
ቸሩ ጌታችንን አቻኩለው ሰቀሉት
እሩህሩሁን ጌታ ቸንክረው ሰቀሉት
ሞትን አስወግዶ ቢሰጣቸው ህይወት(፪)

 እውነት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ
 ዋለ በአደባባይ ሲሰደብ ሲከሰስ
 የሐሰት ዳኝነት አምላክን ወቀሰው
 ህይወት ሰጠን እንጂ ጥፋቱ ምንድን ነው

ስለቸርነቱ ስድብን ከፈሉት
ስለ ርህራሄው የእሾክ አክሊል ሰጡት
ሀሞት እና ከርቤ ሆምጣጤ ደባልቀው
መራራ አስጎነጩት ጨክኖ ልባቸው(፪)

 እውነት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ
 ዋለ በአደባባይ ሲሰደብ ሲከሰስ
 የሐሰት ዳኝነት አምላክን ወቀሰው
 ህይወት ሰጠን እንጂ ጥፋቱ ምንድን ነው

ፈውስን ለሰጣቸው ልባቸውን ሞልተው
አሉት ወንበዴ ነው ስቀለው ስቀለው
ከእጁ በረከትን የተሻሙ ሁሉ
ይጮሁ ነበረ ይገደል እያሉ(፪)

 እውነት ስለሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ
 ዋለ በአደባባይ ሲሰደብ ሲከሰስ
 የሐሰት ዳኝነት አምላክን ወቀሰው
 ህይወት ሰጠን እንጂ ጥፋቱ ምንድን ነው