መዝሙር (እመቤቴ ማርያም እለምንሻለሁ) April 7, 2019



እመቤቴ ማርያም እለምንሻለሁ
በልቅሶ በዋይታ ፊትሽ ወድቄአለሁ
እመቤቴ ስሚኝ ተማጽኜሻለሁ /፪/

ኀዘኔን ጭንቀቴን ለማን እነግራለሁ
ችግሬን ጉዳቴን ለማን አዋያለሁ
እመቤቴ ስሚኝ ተማጽኜሻለሁ /፪/

ኀዘኑ በዛብኝ ፈተናው ከበደኝ
እንደምን ልቻለው እኔስ ደካማ ነኝ
የአማኑኤል እናት ፈጥነሽ ድረሽልኝ/፪/

በጣም ተንገዳገድኩ ልወድቅ ነው እኔ
እመ አምላክ ደግፊኝ ቁሚልኝ ከጎኔ
ምንም አጋር የለኝ ከአንቺ በቀር ለእኔ/፪/