መዝሙር (ወዳንተ እሰግዳለሁ) April 14, 2019



ወዳንተ እሰግዳለሁ ሳለሁ በሕይወቴ
ላንተም እገዛለሁ እስከ ዕለተ ሞቴ
አንተ ነህና መድኃኒቴ የዘለዓለም ቤቴ/፪/

ሳይመሽብኝ ቀኑ ሳይጨልም ድንገት
በጽድቅ ጎዳና ልጓዝ ወደፊት
ምራኝ መንገዱን አሳየኝ እንዳልሳሳት /፪/

የነፍስ የሥጋዬ የህይወቴ ቤዛ
አትበለኝ ችላ በደሌም ቢበዛ
አንተን አምኜ እኖራለሁ ወደየት እደርሳለሁ
አንተን አምኜ እኖራለሁ ወደየት እሄዳለሁ