መዝሙር (አታውኪኝ ነፍሴ) April 14, 2019



አታውኪኝ ነፍሴ አታስጨንቂኝ /፪/
በዓለም መድኃኒት በእግዚአብሔርታመኝ

ዋልያ እንደሚናፍቅ ወደ ውኃ ምንጮች
አቤቱ ወደ አንተ ነፍሴ ናፈቀች

መቼ ተነሥቼ መቼ እደርሳለሁ
የአምላኬንስ ፊቱን መቼ አየዋለሁ

የሕይወትን ውኃ እያስታወሰች
ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች

አታውኪኝ ነፍሴ አታስጨንቂኝ /፪/
በዓለም መድኃኒት በእግዚአብሔር ታመኝ