መዝሙር (አበባ ነሽ ድንግል) November 3, 2019



አበባ ነሽ ድንግል ምሣሌ የሌለሽ
አባ ሕርያቆስ የመሰከረልሽ

በጥሩ መዓዛሽ/2/ አብ እንደወደደሽ

ፍሬሽም ይለያል በብዙ ምክንያት
ከሚያፈሩት ፍሬ ሌሎቹ እጽዋት

በሽታን አጥፍቶ/2/ ስለሚሰጥ ሕይወት

አሁን ግን ከፊቱ ተለወጠ መልክሽ
በግበጽ በረሀ ሙቀት ሲበዛብሽ

ጥምሽን የሚቆርጥ/2/ ውሃ በማጣትሽ

ይሔንን በማሰብ ይሔን በመዘከር
በእለተ ሰንበት በዚህ በጽጌ ወር
ቀርበናል ከፊት/2/ አሁን ለመዘመር