መዝሙር (ዮሐንስ መምህረ ትህትና) November 10, 2019


 ጥርጊያን ያዘጋጀህ ለአዲስ ኪዳን ፍኖት
 መምህረ ንሰሐ መጥምቀ መለኮት
 በምድር የተገለጥክ በኤልያስ መንፈስ
 ልጆችህን ባርከን /፫/ ካህኑ ዮሐንስ

ቀድሞ ያልነበረ ያልተጠራበት ሰው
ስምህን ከሰማይ ያወጣው አምላክ ነው
ነብየ ልዑል ሆይ በማኅፀን ሳለህ
የድንግል ሰላምታ በደስታ አዘለለህ

 ጥርጊያን ያዘጋጀህ ለአዲስ ኪዳን ፍኖት
 መምህረ ንሰሐ መጥምቀ መለኮት
 በምድር የተገለጥክ በኤልያስ መንፈስ
 ልጆችህን ባርከን /፫/ ካህኑ ዮሐንስ

ከሰማይ የመጣው ከሁሉም ይበልጣል
እኔ ከምድር ነኝ ተገዢ ነኝ ለቃል
ብለህ አስተምረህ የጠረግክ ጎዳና
መታዘዝ ያሳየህ መምህረ ትህትና

 ጥርጊያን ያዘጋጀህ ለአዲስ ኪዳን ፍኖት
 መምህረ ንሰሐ መጥምቀ መለኮት
 በምድር የተገለጥክ በኤልያስ መንፈስ
 ልጆችህን ባርከን /፫/ ካህኑ ዮሐንስ

ሴቶች ከወለዱት ከሰው ልጆች መሀል
ፈጽሞ አልተገኘም አንተን የሚመስል
አንተ ነህ ዮሐንስ ከጌታ ፊት ቀድመህ
በንስሐ ጥምቀት ሕዝብን ያዘጋጀህ

 ጥርጊያን ያዘጋጀህ ለአዲስ ኪዳን ፍኖት
 መምህረ ንሰሐ መጥምቀ መለኮት
 በምድር የተገለጥክ በኤልያስ መንፈስ
 ልጆችህን ባርከን /፫/ ካህኑ ዮሐንስ

ቃልህን የሰማው ለኃጢአት ሥርየት
ይጠመቅ ጀመረ የንሰሐን ጥምቀት
ስብከትህን ሰምቶ ሁሉ ተደሰተ
ነቢይም ካህንም ሰማዕትም ነህ አንተ

 ጥርጊያን ያዘጋጀህ ለአዲስ ኪዳን ፍኖት
 መምህረ ንሰሐ መጥምቀ መለኮት
 በምድር የተገለጥክ በኤልያስ መንፈስ
 ልጆችህን ባርከን /፫/ ካህኑ ዮሐንስ

በንጉሥ ፊት እውነት ቢያወራ አንደበትህ
በወጭት ቀረበ ተቆርጦ አንገትህ
አንተማ ዮሐንስ አክሊል ተሸልመህ
በክብር በማዕረግ በሰማይ ቤት አለህ