መዝሙር (በሥጋችን ፈቃድ) March 8, 2020



በሥጋችን ፈቃድ የታሠርን ሁላችን(፪)
ምሕረትን እንለምን(፪) ከቸሩ አምላካችን(፪)
በኃጢአት ብዛት መጎስቆልን አይቶ (፪)
አይጨክንም ጌታ(፪) ይምረናል ራርቶ (፪)
ምንም ብንበድለው ኃጢአት ቢበዛብን (፪)
ታማኝ ነው ጌታችን(፪) ሁሉን ይቅር ሊለን(፪)
ስለዚህ ወገኖች(፪) ክርስቲያኖች ሁሉ(፪)
ንስሐ ለመግባት (፪)ዛሬ ነገ አትበሉ(፪)
ለዓለም ፈቃድ መኖር(2) እንግዲህ ይበቃልና(፪)
ለአምላክ እንገዛ (፪) እንመለስና (፪)
እኛ እንድንታደስ(፪)እንድንሄድ በቃሉ(፪)
በምልጃችሁ እርዱን (፪) ቅዱሳን በሙሉ(፪)