መዝሙር (አንዲት ናት) February 16, 2020


 አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት(፪)
 ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት
 ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት
 ቤተክርስቲያን አንዲት ናት

አዲስ አይደለንም ለመከራው ጉዞ
የወደቀ አናውቅም መስቀል ተመርኩዞ
አምላከ ቅዱሳን ከእኛ ጋር ነውና
በርቱ ክርስቲያኖች በእውነት ጎዳና(፪)

 አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት(፪)
 ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት
 ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት
 ቤተክርስቲያን አንዲት ናት

የአበውን እምነት በአላውያን ፊት
ሰምተን ስላደግን ከገድላት አንደበት
መስዋዕትም ቀርቧል ከፊታችን
እውነት ስትገፋ አይችልም ልባችን(፪)

 አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት(፪)
 ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት
 ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት
 ቤተክርስቲያን አንዲት ናት

አልጠፋችምና በእሳት ተፈትና
ይህን እናውቃለን በገሀድ ነውና
መሰደድ መቃጠል ሁሉም ከጊዜው ነው
ለእውነት ከሆነ ሞትም ክብራችን ነው(፪)

 አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት(፪)
 ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት
 ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት
 ቤተክርስቲያን አንዲት ናት

ከተዋሕዶ ጋር ስላለ መንፈሱ
እውነትን ለማጥፋት መቅደስ አታፍርሱ
በግፍ ቢገደሉም ክርስቲያኖች ሁሉ
ኦርቶዶክስ አትጠፋም ተነግሯል በቃሉ(፪)

 አንዲት ናት ቤተክርስቲያን አንዲት ናት(፪)
 ቋንቋና ዘር ቀለም ማይነጣጥሏት
 ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት
 ቤተክርስቲያን አንዲት ናት

ታሪክን ያኖረች ፊደላትን ቀርጻ
ቅርስን ያወረሰች ገዳማት አንጻ
እንግዳ ተቀባይ መንፈሳዊት እናት
ይህንን አትዘንጉ ኦርቶዶስ አገር ናት
ይህንን አትዘንጉ ተዋሕዶ አገር ናት