መዝሙር (ምን ሰማህ ዮሐንስ) February 7, 2021 (Second Mezmur)

 ምን ሰማህ ዮሐንስ በማኅጸን ሳለህ /፪/
 ሕፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ /፪/
 እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ /፪/
 ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ/፪/

ከተፈጥሮ በላይ ያሰገደህ ክብር
እንዴት ቢገባህ ነው የእናታችን ፍቅር /፪/
ሌላ ድምፅ አልሰማም ከእንግዲህ በኋላ
ለውጦኛልና የሰላምታ ቃሏ /፪/

 ምን ሰማህ ዮሐንስ በማኅጸን ሳለህ /፪/
 ሕፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ /፪/
 እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ /፪/
 ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ/፪/

በረሀ ያስገባህ ለብዙ ዘመናት
ምን ያለ ራዕይ እንዴት ያለ ብሥራት /፪/
አንደ አዲስ ምስጋና ስልቱ የተዋበ
ተደምጦ የማያውቅ ጭራሽ ያልታሰበ /፪/

 ምን ሰማህ ዮሐንስ በማኅጸን ሳለህ /፪/
 ሕፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ /፪/
 እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ /፪/
 ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ/፪/

ከሴት ከተገኙ ከደቂቀ አዳም
ድንግል ስለሆነ በሕይወቱ ፍፁም /፪/
በማኅጸን ሳለ ተመርጦ በጌታ
ለማዳመጥ በቃ የኪዳን ሰላምታ /፪/

 ምን ሰማህ ዮሐንስ በማኅጸን ሳለህ /፪/
 ሕፃን ሆነህ ነቢይ ለክብር የተጠራህ /፪/
 እንደ እንቦሳ ጥጃ ያዘለለህ ደስታ /፪/
 ምን አይነት ድምፅ ነው ምን አይነት ሰላምታ/፪/