መዝሙር (ከሰዎች ማነው) February 14, 2021 (Second Mezmur)

 ከሰዎች ማነው እንደ እኔ ትእዛዝህን ሻሪ/፪/
 ከአማልክትስ ማነው እንዳንተ መሐሪ /፪/

የኃጢአት ሸክም ከብዶብኝ ሲያስጨንቀኝ
ጠላቶች ከበው በእኔ ላይ ቢዝቱብኝ
ብቸኝነቴን አይተህ ስለደረስክልኝ
ተመስገን እንጂ ላንተ ሌላ ምን አለኝ

 ከሰዎች ማነው እንደ እኔ ትእዛዝህን ሻሪ/፪/
 ከአማልክትስ ማነው እንዳንተ መሐሪ /፪/

በደሌን አይተህ በቅፅበት ያላጠፋኸኝ
እንደ ጥፋቴ በቁጣ ያልተበቀልከኝ
ቸር እና የዋህ አምላክ እንዳንተማ አይገኝ /፪/

 ከሰዎች ማነው እንደ እኔ ትእዛዝህን ሻሪ/፪/
 ከአማልክትስ ማነው እንዳንተ መሐሪ /፪/

እንደ ሕዝቅያስ ጸሎቴን አምላክ ስማኝ
እንደ ዳዊት ልመናዬን ተቀበለኝ
በዘመኔ እኩሌታ አምላኬ አትውሰደኝ
ወሰን በሌላት ፍቅርህ ታግሰህ ጠብቀኝ

 ከሰዎች ማነው እንደ እኔ ትእዛዝህን ሻሪ/፪/
 ከአማልክትስ ማነው እንዳንተ መሐሪ /፪/

አዝ = = = /፪/