መዝሙር (ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ) March 14, 2021

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
ለአማልክት አምላክ እናቅርብለት ምስጋና
ምህረቱ ለዘላለም ነውና
ለነገሥታት ንጉሥ እናቅርብለት ምስጋና
የእስራኤል አምላክ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
በጠራንህ ጊዜ ፈጥነህ ድረስ /፫/

 ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
 ተገዙ ለእግዚአብሔር ስሙንም ጥሩ
 ድንቅ ሥራውንም ለአሕዛብ ንገሩ
 የእስራኤል አምላክ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
 በጠራንህ ጊዜ ፈጥነህ ድረስ/፫/

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ
ይመግባልና ሁሉን አስተካክሎ
የእስራኤል አምላክ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
በጠራንህ ጊዜ ፈጥነህ ድረስ/፫/

 ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
 አትወድምና በእውነት
 የሰው ልጆችን ጥፋት
 የእስራኤል አምላክ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
 በጠራንህ ጊዜ ፈጥነህ ድረስ/፫/

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
አቤቱ ጸሎቴን ስማ
በያሬድዊ ዜማ
የእስራኤል አምላክ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
በጠራንህ ጊዜ ፈጥነህ ድረስ/፫/

 ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
 የእስራኤል አምላክ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
 በጠራንህ ግዜ ፈጥነህ ድረስ /፫/
 ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር
 የእስራኤል አምላክ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ
 በጠራንህ ግዜ ፈጥነህ ድረስ /፫/